እንኳን ለ85ኛው የጀግኖች አርበኞች በዓል አደረሳችሁ

ሚያዝያ 27 ቀን ኢትዮጵያውያን ጀግኖች አርበኞች የፋሽስትን ወረራ የቀለበሱበትና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ ያስከበሩበት በዓል ነው። አርበኝነት ማለት ለሀገር ያለ ዋጋ የሚከፈል ከራስ ወዳድነት የነጻ መሥዋዕትነት ነው። ዓላማውም ሀገርንና ሕዝብን ብቻ ማዕከል ያደረገ ነው። ለግል ወይም ለቡድን በተለየ የሚገኝ ነገር የለውም። ለሀገር ከሚገኘው ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና ክብር ከሚደርስ የዜጋ ድርሻ በቀር። እናትና አባት አርበኞች ከፋሺስት…

የዘንድሮው “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖን ለየት የሚያደርገው ምንድን ነው?

‎‎ከመላው የሀገሪቱ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ከ186 በላይ ኢንዱስትሪዎች፤ አዳዲስ ዘርፎች የታከሉበት። ‎ቀደም ሲል ከተከናወኑት ኤክስፖዎች ይበልጥ የገዘፈ፣ የሰፋ እና የደመቀ! ‎ ‎#PMOEthiopia#EthiopiaDelivers ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

የጣና ሐይቅ ተቀድቶ የማያልቅ የልማት ምንጭ፤ የማይደበዝዝ የውበት ጮራ ነው!

ለባሕር ዳርና ለአካባቢው ዘርፈ ብዙ ትሩፋት ይዞ የመጣውን ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ዛሬ መርቀን ለአገልግሎት ከፍተናል። ዳርቻ የለሽ የተፈጥሮ ውበት ከሰው ልጆች ትጋት ጋር ሲደመር ምን ውጤት እንደሚገኝ ባሕር ዳር ማሳያ ናት። በባሕር ዳር በኢትዮጵያ ትልቁ ሐይቅ እና በዓለም ትልቁ ወንዝ የሚገናኙባት ከተማ ናት። ዙሪያዋ ፈጣሪ የሰውን መንፈስ በነፍስም በሥጋም ለማደስ የፈጠረው አካባቢ ነው። በወዲያ…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት !

“የአራት ዓመታት ተከታታይ ጥረት እና የሚጨበጥ ውጤት! ‎በዘንድሮው “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖ ላይ የሀገራዊ ርዕያችንን ተጨባጭ ስኬት መመልከት ትልቅ ክብር ነው። ውጤት ተኮር አመራራችን ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ የኢንዱስትሪ መስፋፋት ተንጸባርቋል። ይኸውም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ በማድረግ፣ ባለፉት አራት አመታት ከ2,800 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ…

የኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ አስደናቂ የሆነ የለውጥ ጉዞ አሳይቷል።

ይህ ጉዞ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ መዋቅር ከግብርና ጥገኝነት ወደ ኢንዱስትሪ በማዞር፣ የውጭ ምንዛሬን በማዳን እና የሥራ ዕድልን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።‎‎ዘርፉ ከሰነቃቸው ዐበይት ዓላማዎች አንዱ፤ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት የንግድ ሚዛኑን ማስተካከል ሲሆን ይህ ጥረት ባለፉት አራት ዓመታት አስደሳች ውጤቶችን አስገኝቷል፦‎‎የውጭ ምንዛሬ ገቢ፦‎የአምራች ኢንዱስትሪው የወጪ ንግድ በ2014 ከነበረበት 358 ሚሊዮን ዶላር፣…

የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ

የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ መዋቅራዊ ማነቆዎችን በመፍታትና የአምራች ዘርፉን አቅም ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ሀገራዊ ብልጽግናን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተደረገ የተቀናጀ ጥረት፣ በዘርፉ የታየው ዕድገትና የተመዘገቡት ስኬቶች የኢንዱስትሪውን መፃኢ ዕድል ብሩህ አድርገውታል።‎‎ዋና ዋና የሥራ አፈጻጸም ስኬቶች፦‎‎ የአምራችነት አቅም ሽግግር‎• አማካይ የማምረት አቅም ከ47% ወደ 67% ከፍ ብሏል።‎• የዘርፉ ዓመታዊ ዕድገት ከ4.8% ወደ 10.7%…

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ማዕከል የመሆን ጉዞዋን አጠናክራ ቀጥላለች።

‎የአሥራ ሦስት ወራት ፀሐይ – በዓመት 13.3 ጊጋ ዋት የሶላር ኃይል በአዳዲስ አምራቾች!‎‎ከዚህ ዐቅም ጀርባ ያሉ ፕሮጀክቶች በምስል ሲቃኙ።‎

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ምርትን ከማሳደግና የውጭ ምንዛሬን ከመታደግ ባሻገር ዕውቀትንና ክህሎትን ለዓለም የምናበረክትበት አዲስ የኢንዱስትሪ ምዕራፍ ተጀምሯል !

ሚያዝያ 25/2018 ዓ.ም የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ፤ 830 ፋብሪካዎችን ዳግም ወደ ስራ በማስገባት፣ 4.85 ቢሊየን ዶላር ገቢ ምርትን በመተካት እና 433 ሚሊየን ዶላር ከኤክስፖርት በማስገኘት አስደናቂ የኢንዱስትሪ ሽግግር ውጤት አስመዝግቧል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት የ”ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄ ሲጀምር፣ ግቡ ምርትን ማሳደግና የውጭ ምንዛሬን መታደግ ብቻ አልነበረም።…

መንግሥት ዘላቂ አጀንዳዎች ላይ በማተኮር ሀገራዊ ብልፅግናን የሚያፋጥኑ መዋቅራዊ ለውጦችን በስኬት እያከናወነ ይገኛል።

ሚያዝያ 24/2018 ዓ.ም የ’ዲጂታል ኢትዮጵያ’ ን መነሻ ያደረገውና ግልጽነትን ያሰፈነው ዘመናዊ የመንግሥት አገልግሎት ሥርዓት፣ በተግባር ፍሬ እያፈራ ያለ ታላቅ ሀገራዊ ሽግግር ነው። በተለይም የቴሌኮም ዘርፍ ሊበራላይዜሽን እርምጃዎች የውድድር መንፈስን በመፍጠር የኢንተርኔትና የዲጂታል ትስስር ተደራሽነትን በከፍተኛ ፍጥነት ማሳደግ ችሏል ። ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍትህን ለማስፈን ወሳኝ የሆነው የ”ፋይዳ” ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓትም በተሳካ ሁኔታ በመተግበር ላይ…