ሦስቱ የመንግሥት ትኩረት አቅጣጫዎች

ታኅሳስ 15/2018 ዓ.ም የኤፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መንግሥት የሀገር ግንባታ ሂደቱን ለማጽናት እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ለሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ዲሞክራሲን መገንባት፣ ተቋማትን ማጠናከርና ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር፡፡ እነዚህ ሦስቱ ምሰሶዎች ሀገራዊ አንድነትን፣ ሰላምና ብልጽግናን፣ እንዲሁም ዜጎች በመተማመን እና በተጠያቂነት ላይ የተመሠረተ የጋራ ራዕይ እንዲኖራቸዉ የሚያደርጉ ቁልፍ መሰረቶች ናቸው፡፡ ዲሞክራሲን የመገንባት ሂደት ለአንድ…

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተጽፈው ለንባብ የበቁት መደመር፣ የመደመር መንገድ፣የመደመር ትውልድና የመደመር መንግሥት መጽሃፍት

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተጽፈው ለንባብ የበቁት መደመር፣ የመደመር መንገድ፣የመደመር ትውልድና የመደመር መንግሥት መጽሃፍት የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞ ከመነሻው ጀምረው እስከ ቀጣይ አቅጣጫዎች በግልጽ ያመላከቱ ናቸው። በመጽሃፍቱ የተነሱ ሃሳቦችም ትናንትን መለስ ብለን እንድንፈትሽ፤ የዛሬ እድልን እንድንጠቀምና ለመጪው ትውልድ ወረትን እንድናሸጋግር መንገድ ያሳዩ ናቸው። ከነዚህም ሶስቱ መጽሃፍት አሁን ላይ ከሕትመት ባሻገር በMedemer መተግበሪያ አማካኝነት በድምጽ ተተርከው ቀርበዋል።…

ፈጠራን መሰረተ ልማት ያደረገ እና በሁሉም መስክ ሉዓላዊ ኢትዮጵያን ለመፍጠር የተነደፈ ሀገራዊ ትልምና ራዕይ ነው

ፈጠራን መሰረተ ልማት ያደረገ እና በሁሉም መስክ ሉዓላዊ ኢትዮጵያን ለመፍጠር የተነደፈ ሀገራዊ ትልምና ራዕይ ነው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ታኅሳስ 14/2018 ዓ.ም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የሀገሪቱን የዲጂታል ሽግግርን በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በመንግሥት አሥተዳደር ማዕቀፍ ዉስጥ ለማካተትና በእስካሁኑ የተመዘገቡ የኢኮኖሚ ስኬቶችን ይበልጥ ለማጠናከር የተነደፈ ሀገራዊ ራዕይ ነዉ፡፡ ዕቅዱ ሁሉን አቀፍ እድገት እና ዓለም አቀፍ…

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጻፉት “መደመር” ፣ “የመደመር መንገድ”፣ “የመደመር ትውልድ” እና “የመደመር መንግሥት” መጻሕፍት

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጻፉት “መደመር” ፣ “የመደመር መንገድ”፣ “የመደመር ትውልድ” እና “የመደመር መንግሥት” መጻሕፍት ሰው ተኮር በሆነ የብዝሃ ኢኮኖሚ ጉዞ ኢትዮጵያን በአጠረ ጊዜ ውስጥ ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር አግዘዋል። በእነዚህ መጻሕፍት የተነሱ እሳቤዎች ከንድፈ ሃሳብ ባሻገር በተግባር የተገለጡና ለትውልዱ ብሩህ ተስፋን ያጎናጸፉ ናቸው። መጻሕፍቱ አሁን ከሕትመት ባሻገር በ Medemer መተግበሪያ አማካኝነት በድምጽ ተተርጉመው ቀርበዋል።…

ሕዝባዊ ዉይይቶች የሰላምና ጸጥታ መሠረት ናቸዉ

ታኅሳስ 13/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ምክንያቱም ከሰላም የበለጠ ምንም ነገር የሌለ በመሆኑ፡፡ ሰላም ለሰው ልጅ እድገትም ሆነ ለሀገር ግንባታ ሂደት ዋንኛዉ መነሻ ነው፡፡ ሰሞኑን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የተደረጉ ሕዝባዊ ዉይይቶች የሕዝብ ድምጽ ጎልቶ እንዲሰማ ማድረጉንና ሕዝቡ ለዘላቂ ሰላምና ልማት ቁርጠኛ መሆኑን የታየበት ሁነኛ መድረክ ነበር፡፡ የዉይይቱ ተሳታፊዎች…

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ሁሉን አቀፍና አካታች የዲጂታል አገልግሎቶች የሚቀርቡበት

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ሁሉን አቀፍና አካታች የዲጂታል አገልግሎቶች የሚቀርቡበት፣ ዜጎችን ማዕከል ያደረገ ስርዓትን በመዘርጋት፣ ሉዓላዊና ደህንነቱ የተጠበቀ አውድን ለመፍጠር ቁልፍ ሚና ይኖረዋል።

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ሶስቱ ግቦች

የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ መንደርደሪያ ያደረገዉ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025”ን ሲሆን በዋናነት ሦስት ግቦችን ለማሳካት ዓላማ ያደረገ ነዉ፡፡ አንደኛዉ ግብ ተደራሽነትን ማስፋት ሲሆን ይህም ሁሉም ዜጎች ከቤታቸዉ፣ ከስልኮቻቸዉ እና ካሉበት ስፍራ ሆኖ የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበትን እድል መፍጠር ነዉ፡፡ ሁለተኛዉ ግብ ለዜጎች እኩል እድል መስጠት ነው፡፡ መንግሥት እኩል እድል ባልሰጠበት ሁኔታ የዜጎች እኩል ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ስለማይቻል ሁሉም…

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ ሁለት መሠረታዊ አስቻይ ጉዳዮች አሉ።

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ ሁለት መሠረታዊ አስቻይ ጉዳዮች አሉ። አንደኛው የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ነው። የኤሌክትሪክ ተደራሽነት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ምግብ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል። የምንጠቀምባቸው የቴክኖሎጂ ጋጄቶች ኤሌክትሪክ ይፈልጋሉ። በመሆኑም በሁሉም አማራጮች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ማስፋት አለብን። ሁለተኛው የኢንተርኔት ትስስር ነው። በርካታ ከተሞች የኢንተርኔት ትስስር ተጠቃሚ ሆነዋል። ነገር ግን በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ይህን ትስስር በሁሉም አካባቢዎች…