ኢትዮጵያ ዜጎችን ከተረጂነት ለማለቀቅ የነደፈችው ስልታዊ ሽግግር ፍሬ እያፈራ ነው!

ሚያዝያ 22/ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ራስን በምግብ ለመቻል የነደፈችው ስትራቴጂካዊ ፖሊሲ ዛሬም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት የማሸጋገር ተከታታይ ስኬቶችን እያስመዘገበ ይገኛል። ይህ ለዘመናት በጠባቂነት ተገድቦ የነበረው ግዙፍ የሰው ኃይል፣ ወደ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት የሚያደርገው ሽግግር በአስተማማኝ መሰረት ላይ ሆኖ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ዛሬ የጀመርነው የፖሊሲ ስኬት፣ የነገዋን በምግብ ራሷን የቻለች ኢትዮጵያን እውን የሚያደርግ እየተፋጠነ ያለ…

የሀገር ውስጥ የነዳጅ አቅርቦትን እንዴት ማስቀጠል ተቻለ? የኢትዮጵያ አየር መንገድስ በአለም አቀፉ የነዳጅ ቀውስ እንዴት ሥራ አላቆሙም ? ኢትዮጵያዊያን ይህንን ጥያቄ ሊጠይቁ ይገባል !!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መንግሥት የሚከተለው የጠራና ስትራቴጂካዊ ፖሊሲ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰቱትን ፈታኝ የኢኮኖሚና የነዳጅ ቀውሶች በጽናት እንድትመክት የሚያስችል ጠንካራ ሉዓላዊ አቅም አጎናጽፏታል። ይህ ሀገራዊ የጽናት ልዕልና በተጨባጭ የታየው እንደ ሊፍታንዛ ያሉ ግዙፍ የአውሮፓ አየር መንገዶች በነዳጅ እጥረት አቅም አንሷቸው በረራ እስከመቀነስና ሌሎች ሀገራት ደግሞ በአጭር ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ በረራ ለማቋረጥ…

ከቀውስ ባሻገር መሻገር !!!

ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነትና በሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት ምክንያት ዓለም አቀፉ የነዳጅ አቅርቦት ተቋርጦ፣ የበርካታ ሀገራት ማደያዎች እየተዘጉና ማኅበራዊ ቀውሶች እየተባባሱ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ በተወሰነም ደረጃ ቢሆን ይህንን ከባድ ፈተና መቋቋም የቻለችው መንግሥት ላለፉት ስምንት ዓመታት በታዳሽ ኃይል (ውኃ፣ ነፋስ፣ ፀሐይና ጂኦተርማል) ላይ ባከናወናቸው ግዙፍ ስትራቴጂያዊ ፕሮጀክቶች ነው። የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የተለያዩ የኃይል አማራጮችና የኤሌክትሪክ…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

‎”የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውና በማህበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የቀረቡበት የምክክር መድረክ ተገኝቼ ሃሳቤን አጋርቻለው። ‎‎የማህበራዊ ዘርፍ ግንባታ እንደ ሌሎች መሠረተ-ልማቶች ውጤቱ ወዲያው የሚታይና የሚጨበጥ ባይሆንም፣ ለሀገር ዘላቂና ወሳኝ መሰረት የሚጥል ነው። ኢትዮጵያ በሚገጥሟት ተግዳሮቶች ሳትገደብ ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባች ሲሆን፣ ምንም እንኳ የዐቅም ውስንነቶች ቢኖሩብንም ለማሻሻል…

‎የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውና በማህበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የቀረቡበት የምክክር መድረክ፤ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።

‎በዚህም ባለፉት ዓመታት በማህበራዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ወሳኝ ስኬቶች ቀርበዋል። ‎በስምንት የለውጥ ዓመታት፤ ኢትዮጵያ በመሰረታዊና ማህበራዊ ዘርፎች የተስተዋሉ ክፍተቶች ላይ ትኩረት በማድረግ፤ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ሰፊ ሥርዓታዊ ሽግግር አድርጋለች። ‎በትምህርት ዘርፍ አዲስ ሥርዓተ-ትምህርትን በመተግበር፣ የመማሪያ መጽሐፍት ስርጭትን በማሻሻል እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርትና የሀገር አቀፍ ፈተና ሥርዓቶችን በማዘመን፣ የትምህርት ዘርፉ ጥራትና ተዓማኒነት እንዲላበስ ተደርጓል። ‎በተመሳሳይ የጤናው ዘርፍ ለ30…

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በሚኒስትር መስሪያቤታቸው የተመዘገቡ ዐበይት ስኬቶችን አቅርበዋል።

‎በዚህም ዘርፉ ከለውጡ በፊት ሲቸገርበት የነበሩ መጠነ ሰፊ ክፍተቶችን በመለየት ፈጣን መፍትሔ በመስጠት ሰፊ ስኬቶችን አስመዝግቧል።‎‎ከተገኙ ስኬቶች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦‎የፖሊሲና የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት የዜጎችን መብት ጥበቃ፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ። አደረጃጀቶችን በመደገፍና በማጠናከር መብትና ግዴታ በማወቅ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ የአቅመ ደካማ ዜጎችን የመደገፍና የማገዝ ባህል ማሳደግ ጥቂቶቹ ናቸው።‎እነዚህ ስኬቶች ቁጥር ብቻ ሳይሆኑ በተጨባጭ 4,330,948 የሚሆኑ…