የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“‎በዛሬው እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት የቀረቡትን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን አጽድቋል። ‎‎ሹመት የምንዝናናበት ሳይሆን የምንፈጋበት፣ የምንሰራበት፣ ኢትዮጵያን ለማጽናት፣ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ፣ ኢትዮጵያን ወደ ስልጣኔ ጉዞ ለማስኬድ ከፍተኛ ጥረት የሚደረግበት መስክና የሀገር ትልቅ አደራ ነው። ‎‎በሚቀጥሉት ዓመታት ኢትዮጵያ በውሳኔዋ ሉዓላዊ፣ በልዩነት ውስጥ የተሳሰረች፣ እሴት በመፍጠርና ጠብቆ በማቆየት ረገድ ምርታማ፣ ቀጣናዊና አህጉራዊ መልህቅ በመሆን የምትመራ፣ እንዲሁም…

በተጨማሪም በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፦

1) ክቡር አቶ አደም ፋራህ በም/ጠ/ሚ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ አስተባባሪ 2) ክቡር አምባሳደር በትረ መንግስቱ የጠ/ሚ ጽ/ቤት ሃላፊና የካብኔ ጉዳዮች ሚኒስትር 3) ክብርት ወ/ሮ እናትአለም መለሰ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር 4) ክቡር አቶ ፍቃዱ ተሰማ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር PMOEthiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረቧቸው ዕጩዎች ዛሬ ጠዋት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚከተለው ፀድቀዋል፦

የመደመርመንግሥት PMOEthiopia

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“በኢትዮጵያ ለሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት እና የላቀ አመራር ልምድ ልውውጥ ላይ የሚሳተፈውን ልዑክ ከመሩት የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ጋር ተወያይተናል። ‎ኢትዮጵያና ናይጄሪያ የበርካታ ብሔረሰቦች፣ የብዙ ባህሎች እና የከፍተኛ ሕዝብ ቁጥር ባለቤት የሆኑ ሀገራት ናቸው። ይህም የሁለቱን ሀገራት ትብብር አጠናክረን ለማስቀጠልና የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ መልካም ዕድል ይሰጠናል።” ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

የመደመር መንግሥት

“በግንባርም፣ በሚዲያም፣ በሰይፍም በሰልፍም ፣ በውሸትም፣ በሀሜትም፣ በተንኮልም፣ በሽረባም፣ ባገኙት የትግል ሜዳ ሁሉ ከጉዟችን ሊያደናቅፉን መከራቸውን አዩ፤ ኢትዮጵያን ግን አልቻሏትም፤ አይችሏትም!” -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #የመደመርመንግሥት#PMOEthiopia

የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊሆን አይችልምና በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ተግተን እንሠራለን።

የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊሆን አይችልምና በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ተግተን እንሠራለን።

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #የመደመርመንግሥት#PMOEthiopia

አዲሱ የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ሲመሰረት፤

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም በሀገሪቱ የተካሄደው ምርጫ እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትኖ ያለፈ እና በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ባህል ያጠናከረ መሆኑን ገልጸዋል። በዲሞክራሲያዊ ውድድር ውስጥ የፓርቲዎች ማሸነፍና መሸነፍ ቢኖርም ኢትዮጵያ ግን አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ልጆች የሌሏት ሀገር መሆኗን አፅንኦት ሰጥተዋል። እንደ ሀገር የገጠሙንን ፈተናዎች ማሸነፍ የምንችለው እጅ ለእጅ ተያይዘን እንደ ወንድማማች…