የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም. በይፋ ይመሰረታል

‎‎‎ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በስኬት መከናወን ተከትሎ፤ አዲሱ የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም. በይፋ ይመሰረታል።‎ ‎ኢትዮጵያ- አዲሲቷ የተስፋ አድማስ‎ ‎#PMOEthiopia#የመደመርመንግሥት ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

“የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሰበሰቡ የአጀንዳ ነጥቦችና ምክረ ሐሳቦችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፣ ለፌደራል እና ለክልል መንግሥታት በይፋ አስረከበ”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል አመራሮች በተገኙበት በተካሄደ መርሃ ግብር፤ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከብሔራዊ ምክክሩ የተገኙ የአጀንዳ ነጥቦችንና ምክረ ሐሳቦችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም ለፌደራል እና ለክልል መንግሥታት ዛሬ በይፋ አስረክቧል። ‎‎ይህ የሰነድ ርክክብ፤ በምክክርና በሰላማዊ መንገድ የኢትዮጵያን የቆዩ ሀገራዊ ፈተናዎች መፍታት አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ፤ በመደመር መንግሥት ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍ…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“ኢሬቻ ሰላም ነው! ገዳ ስልጣኔ ነው! የኢትዮጵያ ስልጣኔ አይቀሬ ነው! እንኳን የክረምቱን አስቸጋሪ ወቅት በሰላም አሳልፋችሁ ለብሩሁ ብራ አደረሳችሁ። የክረምቱ ጨለማ አልፎ የብራዋ ጀንበር ስትወጣ ኦሮሞ በአንድነት ወጥቶ በባህሉ ስርዓት ወደ መልካ ይሄድና የክረምቱን ጨለማ ያሳለፈውን ፈጣሪውን ያመሰግናል። ለሚመጣውም ጊዜ ተስፋን ይሰንቃል። አባቶች “ማሬሆ” እናቶች ደግሞ “አራሮ” በማለት ለቸሩ አምላክ ምስጋና ያቀርባሉ። ወደ መልካው በመውረድም…

|

ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን እንዲዘጋ ወሰነች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአስመራ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለመዝጋት መወሰኑን አስታውቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ከኤርትራ በኩል ለተሰነዘሩ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ላልሆኑ ጠብ ጫሪ እና የጠላትነት ድርጊቶች የአጸፋ ምላሽ በመስጠት፣ በኤርትራ አስመራ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲውን ለመዝጋት ውሳኔ ማስተላለፉን ገልጿል። ሚኒስቴሩ አያይዞም የቪዬና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ስምምነት ድንጋጌዎችን በመጣስ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ላይ ቀጥተኛ አደጋ በሚፈጥሩ…

የወርሀ ነሐሴ እና መስከረም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት

አረንጓዴ ዐሻራ፦“ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ ተሳትፈዋል። ማኅበራዊ ጉዳይ፦ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመትን እና የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነሥርዓት፤ የአፍሪካን የኢንዱስትሪ አቅም ለማሳደግ፣ መጠነ ሰፊ እድሎችን ለመፍጠር እና በመላው ምስራቅ አፍሪካ ለላቀ ኢኮኖሚያዊና የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነትን መሰረት ለመጣል ትልቅ እርምጃ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሁነት ነው። ‎‎በአህጉራችን የምትገኙ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ ባለሀብቶች እና ስራ ፈጣሪዎች፤ በአፍሪካ ላይ ኢንቨስት ልታደርጉ፣ ባለን አቅምና የጋራ ጸጋ እምነት ሊኖራችሁ እንዲሁም አህጉራዊ መፃኢ እድላችንን የሚወስኑ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ጣቢያ የመሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓትን ለመካፈል ዛሬ ጠዋት ኬንያ ገብተዋል።