“ከአለም ባንክ ፕሬዝደንት እና ከኢትዮጵያ መልካም ወዳጅ አጄይ ባንጋ ጋር መወያየት ሁልጊዜም ቢሆን አስደሳች ነው። በመካሄድ ላይ ስላሉት በአለም ባንክ ቡድን ለኢትዮጵያ የሚደረጉ ድጋፎች ዙሪያ ተወያይተናል። ይኸውም በጤና፣ በኃይል ምንጭ እና የአየር ንብረት ጥበቃ የልማት ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ ጉዳይን የተመለከተ ነበር። Always a great pleasure meeting with Ajay Banga, President of the World Bank and…
“ከዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታመር ጋር ተገናኝተን በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ጠንካራውን እና ለረጅም ዘመናት የቆየውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደፊት ማራመድ በማስፈለጉ ላይ ተወያይተናል። Met with Sir Keir Starmer, Prime Minister of the United Kingdom for exchanges on the need to take forward the strong and longstanding bilateral relations between two countries.” Prime Minister Abiy Ahmed…
“በቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ ከኢንዶኔዥያ ምክትል ፕሬዝደንት ጊብራን ራክቡሚንግ ራካ ጋር መልካም ውይይት አድርገናል። በሁለቱም ሀገሮቻችን ቅድሚያ በምንሰጠው በንግድ እና በምግብ ሉዓላዊነት ላይ ባተኮረ የግብርና ማዘመን ሥራ ትብብራችንን ለማጠናከር የሚያስችሉ መንገዶች ላይ ተነጋግረናል። Good conversation with Vice President Gibran Rakabuming Raka of Indonesia at the G20 Summit. We explored ways to strengthen the cooperation of…
“በቡድን ሃያ መሪዎች ስብሰባ ፍሬያማ እና ትርጉም ያላቸው ተጨማሪ ውይይቶችን ከህንድ፣ ቬይትናም፣ ደቡብ ኮሪያ እና አውስትራሊያ መሪዎች ጋር አካሂደናል። A productive and substantive day at the G20 Leaders’ Summit with additional engagements with fellow leaders from India, Vietnam, South Korea and Australia as well.” Prime Minister Abiy Ahmed Ali (PHD)
“የጀርመን ቻንሰለር ፍሬድሪክ ሜርዝ ጋር ተገናኝተን ተወያይተናል። ውይይታችን በቁልፍ የጋራ ፍላጎት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን ትስስራችንን ለማጠናከር የሚረዱ መንገዶችን ለመፈለግ ያለንን ፍላጎት ገልጸናል። Good to meet with Chancellor Friedrich Merz today. We exchanged views on key areas of mutual interest and expressed our shared intention to explore ways to strengthen ties.” Prime Minister Abiy Ahmed…
ከፊንላንድ ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር በቀጠናዊ፣ ባለብዙ ወገን ትብብር፣ እና በሁለትዮሽ ግንኙነት በትምህርት ፣ የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ እና በኢትዮጵያ በተከፈተው የኢኮኖሚ ምኅዳር ስላሉ የኢንቨስትመንት እድሎች ተወያይተናል። ውይይታችን የሁለትዮሽ ትስስራችንን እና የጋራ ጥቅም ትብብሮችን በማጠናከር ላይ ያለንን አቋም ያጠናከረም ነበር። Met with President Alexander Stubb of Finland for bilateral discussions on regional issues, multilateral cooperation,…
ከቱርክዬ ፕሬዝደንት ጣይብ ኤርዶዋን ጋር በኢኮኖሚ፣ የባሕል ወዳጅነት ግንኙነት፣ ዘላቂ ልማት፣ በአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን በሚያካትቱ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል። Productive meeting with President Recep Tayyip Erdoğan of Türkiye on a range of topics, including economic and cultural partnerships, sustainable development, and cooperation on climate action.
“ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን የአቡዳቢ ልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ ካሌድ ቢን መሃሙድ ቢን ዛይድ አልናህያን ጋር የመወያየት እድል አግኝተናል። ውይይታችን ስትራቴጂካዊ ትብብራችንን በማጠናከር ለበለጠ የጋራ ርምጃ እድሎችን መመልከት ላይ ያተኮረ ነበር። On the sidelines of the G20 Summit, I also had the honor of meeting with Sheikh Khaled bin Mohamed bin Zayed Al Nahyan, Crown…
“ክቡር የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም ለሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወደ ምድረቀደምት ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ። ጉብኝትዎ በማሌዢያ እና ኢትዮጵያ መካከል እያደገ ያለውን ወዳጅነት እና ትብብር የሚያሳይ ሲሆን በሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ውስጥም በጠቃሚ ጊዜ የተደረገ ጉብኝት ነው።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
