ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚላመድና የማይበገር የልማት ግስጋሴዋን በተጨባጭ ውጤቶች እያስመሰከረች ቀጥላለች።
ይህ ጉዞ በተቀናጀ አሰራር ተመስርቶ፣ ከመቀነስ እስከ መቋቋም ድረስ የሚያካትት የልማት እርምጃዎችን በአስተማማኝ መንገድ አቀናጅቷል። የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቀነስ የካርቦን ልቀትን መቆጣጠር፣ የደን ጭፍጨፋን በመከላከል እና በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር 48 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የሀገሪቱን አረንጓዴ ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል። በተመሳሳይ ጊዜ የውሃ አስተዳደርን ማዘመን እና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተስማማ ግብርናን በመተግበር በምግብ ዋስትና…

