ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው !

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው ! የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጥቅምት 22/02/2018 መንግሥት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት እንዲቻል የተኪ ምርት ስትራቴጂን በመቅረጽ ወደ ሥራ በመግባቱ ከፍተኛ ውጤቶች ተመዝገባዋል ። ስትራቴጂው የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲኖር፣ የወጪ-ገቢ ምርት እንዲመጣጠን እና ሀገራዊ ሉዓላዊነትን እንዲረጋገጥ እያደረገ ይገኛል ። በተለይ በውስጥ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመስከረም እና ጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም በመሠረተ ልማት፣ በገጠር ልማት፣ በአስተዳደራዊ ማሻሻያ እና በዲፕሎማሲያዊ ትብብር ላይ ያተኮሩ ተከታታይ አገራዊ እና ዓለም አቀፍ ተግባራትን አካናውነዋል። ያለፈውን ወር ተግበራት በጨረፍታ እነሆ፥

የከተማ ልማት እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በተመለከተ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር ለሚገነባው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና በጎልደን ኮንኮርድ ግሩፕ አማካኝነት ለሚገነባው የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ መሠረት መጣላቸው ከካናወኗቸው ቀዳሚ ተግባራት የሚጠቀሱ ናቸው። የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ከሂላል የነዳጅ ስፍራ ድፍድፍ ነዳጅ በማውጣት፣ በማጣራትና በማጠራቀም በአመት 3.5 ሚሊዮን ቶን…

የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ንረትን ለመቀነስ መንግሥት ምን አደረገ ?

“የኑሮ ውድነት የበርካታ ሀገራት ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በአንዳንድ ሀገራት ከ400 ፐርሰንት በላይ የደረሰ የዋጋ ንረት እየተመዘገበ ነው፡፡ ከአፍሪካም 172 ፐርሰንት የደረሰ የዋጋ ንረት ያጋጠመ ሲሆን በጎረቤት ሀገራት እንኳን 72 ፐርሰንት የደረሰ የዋጋ ግሽበት ተመዝግቧል ። ከለውጡ ወዲህ መንግሥት አለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ቀድሞ በመገምገም ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ውድነት ጫናን በዘላቂነት ለመቀነስ በርካታ ኢንሼቲቮችን ቀርጾ…

“የገጠር ሽግግርን ለማረጋገጥ አንዱ መንገድ የእርሻ ማሽነሪዎችን ማበራከት ነው ።”ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

በግብርናው ዘርፍ ያሉ አቅሞችና ጸጋዎችን ለይቶ በማልማት የአርሶደሩን ህይወት የሚቀይር መዋቅራዊ ሽግግር እየተደረገ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“ዛሬ በምስራቅ ሸዋ ዞን የነበረን ጉብኝት በክረምት የስንዴ ምርት ሥራዎች የተገኘውን ውጤት የምርት አሰባሰቡን በመመልከት ለመገምገም እና የበጋ ስንዴ ሥራ ማስጀመር ላይ ያተኮረ ነበር። በዚያው አካባቢ የሙዝ፣ ፓፓያ እና አሳ ክለስተር ሥራዎችንም ተመልክተናል። ነባሩ ባሕላዊ የግብርና ዘዴ አሁንም ያለ ቢሆንም በሰፊው ለማረስ የሚያስችለው ሜካናይዜሽን እያደገ በመሄዱ የአካባቢውን የግብርና ብቁነት እና ምርታማነት እያሳደገ ይገኛል። ወደኋላ መለስ…

የፖለቲካ ሥልጣንን በተመለከተ

“ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያስፈልገው ብቸኛው መንገድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ነው፡፡ ችግሮች አሉኝ የሚሉ አካላት ጋር ቁጭ ብሎ በመነጋገር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አሁንም በራችን ክፍት ነው። የኢትዮጵያን እድገት የማይሹ ሀገራት በጦርነት እንደማያሸንፉን ያውቁታል፡፡ ያላቸው ምርጫ ባንዳዎችን መላክ ነው። ኢትዮጵያን በቅጡ ያላወቁ የውስጥ ባንዳዎች ደግሞ ከጠላት ጋር በማበር ዓላማቸውን የሚያሳኩ ይመስላቸዋል፡፡ ይህ ፈጽሞ ሊሳካ አይችልም። “ ጠቅላይ…