የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት !
“ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት፤ የጋራ ታሪክ፣ የአሁን እና ተሻጋሪ ትብብር ፣ በሰላም አብሮ ለመኖር!
“ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስምንት አስርት ዓመታት ጉዞን ምክንያት በማድረግ፣ “በሰላም አብሮ ለመኖር” በሚል መሪ ቃል ልዩ የመታሰቢያ ቴምብር ስብስብ አውጥታለች።
እነዚህ አራት ቴምብሮች እ.ኤ.አ. በ1945 በሳን ፍራንሲስኮ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን ከመፈረም ጀምሮ፣ በኮንጎ የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን እስከማሰማራት እና በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውን የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እስከ ማስተናገድ ያለውን የጋራ ታሪካችንን የሚተርኩ ናቸው። በዓለም የፖስታ ህብረት በኩል ለ192 ሀገራት የተሰራጩት እነዚህ ቴምብሮች፣ ለአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን ለትውልድ ሁሉ የሚተርፍ የታሪክ ዐሻራ ማሳያ ናቸው።
በዚሁ አጋጣሚ፣ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ክቡር አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና ለቡድናቸው፣ በዘመናዊው ታሪክ ውስጥ እጅግ ፈታኝ በሆነ ወቅት ላይ ሰላምን፣ ልማትን እና ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር እያሳዩት ላለው ጽኑ አመራር ጥልቅ አድናቆታችንን እንገልጻለን።
የተባበሩት መንግሥታት የጸናው ሀገራት ከመከፋፈል ይልቅ ውይይትን ስለመረጡ ነው።
ኢትዮጵያም ይህንኑ የሁልጊዜ ምርጫዋን ታጸናለች!”
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication
See less











