ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እድሳት የተደረገለትን የፋሲል ግቢ በሚመርቁ ወቅት ያስተላለፉት መልዕክት:-
የጎንደር ህዝብ ታላቅ በሆነው በዚህ ደስታው ተካፋይ እንድንሆን ስለፈቀደልን እናመሰግናለን ። ጎንደር ሽማግሌዎች አሏት ባዕድ ሳይሆን ባላገሮች፣ ባለቤቶች እንኳን ከአንድ ሰፈር ወደ ሌላ ሰፈር ተንቀሳቅሰው የሀገራቸውን ልማት ማየት፣ ማገዝ እንዲችሉ ሰላም ያስፈልጋል ። የወጡ ወንድሞቻችን ጊዜ ማባከን የለባቸውም፤ የሚያስፈልገን ተመልሰው በአንድነት እና በትብብር መሥራት፣ ሀገር ማልማት አለብን ። ዛሬ ጎንደርን፣ ባሕርዳርን ወይም አማራ ክልልን ከአማራ…

