የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
የኅብር ቀን “ኢትዮጵያችን በሀገር በቀል እሴቶቿ፤ የነገውን ብሩህ ተስፋዋን በገዛ እጆቿ እየቀረጸች ትገኛለች! በትውልድ ቅብብሎሽ ያገኘናቸውን ድንቅ የሀገር በቀል እሴቶቻችንን በማጎልበት እና በመደመር ፍልስፍና በመመራት፣ ለጽኑ ኅብረብሔራዊ አንድነታችን የማይናወጥ መሠረት ጥለናል። ታሪካዊውን ሀገራዊ ምክክር የመጀመር የታሪክ እጥፋት ተነስተን፣ የሁሉም ዜጎቻችንን ሕይወት ከሚለውጡ ሰው-ተኮር የኮሪደር ልማታችን፣ የበጎ ፈቃድ ስራዎቻችን እንዲሁም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብርን በተግባር እውን እስከማድረግ…
