የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ስምምነት ዛሬ አከናውነናል። ‎በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ…

የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዓመት ማብሰሪያና የጳጒሜ ቀናት አከባበር መርሃ ግብር አስመልክቶ ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ!

የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዓመት ማብሰሪያና የጳጒሜ ቀናት አከባበር መርሃ ግብር አስመልክቶ ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ!

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።

ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶችን እንዳስመዘገበች የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡ አገልግሎቱ የዘንድሮ የጳጒሜን ቀናት የሚከበሩበትን ዓውድ፣ የቀናቱን ስያሜ እና መሪ መልእክት ይፋ ያደረገበትን መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫዉን የሰጡት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ “ጳጒሜን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ወር ብሎ ለማክበር የሚያስችሉ ስኬቶች እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት መመዝገባቸውን…

ከውስጣዊ ዐቅም ትንሣኤ እስከ ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት፡ የኢትዮጵያ የጽናት ምዕራፍ!

ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን እና ጂኦ-ፖለቲካዊ ጫናዎችን በጽናት በመመከት፣ ፈተናን ወደ ታሪካዊ ዕድል መቀየር የሚቻለው በውስጣዊ ዐቅም ልዕልና እንጂ በውጭ ጥገኝነት እንዳልሆነ በተግባር አሳይታለች። መንግሥት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የነደፋቸው የልማት እና የሪፎርም ማዕቀፎች ሀገሪቱን ከውጭ ተጽዕኖዎች በሂደት በማላቀቅ፣ በማንኛውም ፈተና ውስጥ የማይበገር ሁሉን አቀፍ ሉዓላዊነት እንዲገነባ መሠረት እየጣለ ይገኛል። በግብርናው ዘርፍ…

የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት

የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር፦ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስምንተኛ ዓመቱን በያዘበት በዚህ ዓመት፤ የኮፕ32 (COP32) ሰብሳቢ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የኮፕ32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ዓመታዊውንና የአንድ ጀምበር ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን መርተዋል። ዘመቻው በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአንድ ቀን ውስጥ 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታላቅ…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

#ኢትዮጵያ በአኒሜሽን ጥበብ፤ ‎ እጅግ ማራኪ ውበት፣ የማይደበዝዝ የታሪክ ትውፊት እና ድንቅ ብዝሃነት ያላት ምድር። ‎‎የሀገሬ ልጆች የኢትዮጵያን ድንቅ የብዝሃነት ውበት ትጎበኙ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ! #LandOfOrigins#VisitEthiopia

ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖዋ እያደገ፤ ስትራቴጂካዊ ጥያቄዎቿም ተቀባይነት እያገኙ ቀጥለዋል!

ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ በሰላም፣ በጋራ ተጠቃሚነት እና በሉዓላዊነት መከበር ላይ የተመሠረተ ውጫዊ ግንኙነቷ ዛሬ ላይ ከየትኛውም ጊዜ በላቀ መልኩ ተጨባጭ ድሎችን እያስመዘገበ ይገኛል። ሀገራችን በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ መድረኮች ያላት አቋም እየተከበረ፣ የዲፕሎማሲ ተጽዕኖዎቿም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፉ መጥተዋል። ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት እና በሰላም አስከባሪነት፣ በሽብርተኝነት ትግል እንዲሁም በቀጣናዊ መረጋጋት ግንባር ቀደም…