ዛሬ ማለዳ በባሌ ዞን፣ ደሎ መና ወረዳ በመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አማካኝነት የተጀመረውን የወልመል ወንዝ መስኖ ልማት ፕሮጀክትን መርቀናል። ፕሮጀክቱ የወልመል ወንዝን በመስኖ በሚገባ በመጠቀም የግብርና ምርታማነትን በማላቅ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተከናወነ ነው። ፕሮጀክቱ ዘላቂ የገጸምድር የመስኖ ሥርዓት በመገንባት የግብርና ስራው ለዘመናት በዝናብ ውሃ ላይ ተመስርቶ የነበረውን የአካባቢውን ሕዝብ ዘላቂ የኑሮ ዘዴ ለማጎናፀፍ ታልሞ ተከናውኗል።
ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ተግባር በሚገባበት ወቅት 20,000 ለሚሆኑ አርሶአደሮች ለሚያገለግል 9687.45 ሄክታር የእርሻ መሬት አስተማማኝ የመስኖ አቅርቦት ይኖረዋል። ይኽም የግብርና ምርታማነትን የሚያሳደግ፣ ለድርቅ የማይበገር ከባቢን የሚፈጥር ብሎም በማኅበረሰቡ አዳዲስ የሥራ እድል የሚፈጥር ይሆናል። ከነዚህ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ባሻገር የአካባቢውን የውሃ አስተዳደር ተቋማትን በማጠናከር፣ የአካባቢውን ሕዝብ ባለቤትነት በማሳደግ ብሎም የወልወልን ወንዝ ዘላቂ አጠቃቀም በማጎልበት የተሻለ የምግብ…
