ዳግም ግጭት እንዳይፈጠር የሃይማኖት አባቶች፣ ባለሀብቶች፣ ምሁራን እና ኤምባሲዎች የበኩላቸዉን ሚና እንዲወጡ መንግሥት አሳሰበ፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ያስገኘዉ ሰላም ዘላቂነት እንዲኖረዉ እና የክልሉ ሕዝብ ሰላም፣ ልማት እና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲመለሱ ባለድርሻ አካላት ሚናቸዉን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በመገኘት ለምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ አንጻራዊ ሰላም መኖሩንና መጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ “በፕሪቶሪ የተደረሰዉ የሰላም…
