የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼኽ ሞሃሙድን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ተቀብያለሁ

“የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼኽ ሞሃሙድን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ተቀብያለሁ። ባለፈው አንድ አመት እየሰራንባቸው የቆየነውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ውይይቶች በመቀጠል ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። የሃሳብ ልውውጣችን የወል የቅድሚያ ጉዳዮቻችንን ለመከወን ብሎም ለጠንካራ ግንኙነት፣ ቀጠናዊ መረጋጋት እና ልማት ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያፀና ነበር።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

የመደመር እሳቤ ከሥልጣኔ አድማስ እስከ ኢኮኖሚያዊ ፍትሐዊነት፣

የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የመደመር እሳቤ (Synergy) በሕንድ የታወቀ መሆኑን መግለጻቸው፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፍልስፍና አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትን የሚያሳይ ሲሆን ይህ እሳቤ ከጥንታዊ ሥልጣኔ ዕሴቶች ተነስቶ እስከ ዘመናዊ የኢኮኖሚ አስተዳደር ድረስ ያለውን ጉዞ መተንተን ይቻላል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ለእያንዳንዱ ሀገር ዕድገት እርስ በእርስ መተማመንና በጋራ ጥረት በአብሮነት መጓዝ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ሐሳብ የመደመር…

“ልክ እንደ ሕንድ፣ እራሳችንን ከውስጥ በማጠናከር እና ከአለም ጋር በመተሳሰር እናምናለን።”

“ልክ እንደ ሕንድ፣ እራሳችንን ከውስጥ በማጠናከር እና ከአለም ጋር በመተሳሰር እናምናለን።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ህብረት አፍሪካን በሚገባ የሚወክል ኮፕ 32 ለማዘጋጀት እንዴት ተቀራርበው መስራት እንደሚችሉ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር እና ከቡድናቸው ጋር ውይይት አድርገዋል

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ህብረት አፍሪካን በሚገባ የሚወክል ኮፕ 32 ለማዘጋጀት እንዴት ተቀራርበው መስራት እንደሚችሉ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር እና ከቡድናቸው ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም በክቡር ማህሙድ አሊ የሱፍ መሪነት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን COP32ን የተሳካ ለማድረግ የኢትዮጵያ ቁልፍ አጋር ለመሆን ቁርጠኛ መሆናቸውን መግለጻቸውን አስታውቀዋል።

የመደመር እሳቤ

“የመደመር እሳቤ ከህንድ ልምምድ ጋር የሚመሳሰል በኢትዮጵያው ላሊበላ እና በሕንዱ ታሚናል ፍልፍል አለቶች መካከል እንዳለው መወራረስ ያለ ነው።” ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

“በአንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን ህንዳውያን ስም የወዳጅነት ሰላምታ፣ መልካም ምኞት፣ ወዳጅነት እና ወንድማማችነትን አምጥቼላችኋለሁ!”

ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንድ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ዛሬ በቤተ መንግሥት ያደረጉላቸው አቀባበል።

#PMOEthiopia https://www.facebook.com/share/v/1AD7SbZuJa ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

የኢትዮጵያና ሕንድ የቆየ ድፕሎማሲዊ ግንኙነት የአፍሪካ ሕንድ ግንኙነት ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው

ታኅሳስ 7/2018 ዓ.ም የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከታኅሳስ 7-8/2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ ይህም የሁለቱን ሀገራት የቆየ ድፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነዉ፡፡ ጉብኝቱ ኢትዮጵያ በሕንድ የአፍሪካ ፖሊሲ ማዕቀፍ ውስጥ ያላትን እየጨመረ የመጣውን የኢኮኖሚ ትስስር፣ የሁሉ አቀፍ ልማትና ስትራቴጂካዊ ትብብር፣ እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የሚያጎላ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር ዋንኛ ዲፕሎማሲያዊ ማዕከል…

ሀገር ሚያሻግሩ 3 የልማት አምዶች!

የኢትዮጵያ መንግሥት ላለፉት ዓመታት የወሰዳቸው እርምጃዎች፣ የኢኮኖሚ ጥንካሬን ከዴሞክራሲያዊ ምህዳር መስፋፋትና ከአዎንታዊ የዓለም አቀፍ ገጽታ ግንባታ ጋር ለማጣመር የተደረገ ጥረት ሲሆን ይህ የለውጥ ጉዞ ለቀጣይ የሀገሪቱ ዕድገት ወሳኝ ምዕራፍ ነው። የመጀመሪያው የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት፣ ከእድገት ወደ ጥራት የሀገር አቀፍ ልማት በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን የሚያሳዩት እርምጃዎች፣ የኢኮኖሚ ዕድገቱን ከመጠን (Quantity) ወደ ጥራት (Quality) ለማሸጋገር ያለመ…