የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ሶስቱ ግቦች
የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ መንደርደሪያ ያደረገዉ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025”ን ሲሆን በዋናነት ሦስት ግቦችን ለማሳካት ዓላማ ያደረገ ነዉ፡፡ አንደኛዉ ግብ ተደራሽነትን ማስፋት ሲሆን ይህም ሁሉም ዜጎች ከቤታቸዉ፣ ከስልኮቻቸዉ እና ካሉበት ስፍራ ሆኖ የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበትን እድል መፍጠር ነዉ፡፡ ሁለተኛዉ ግብ ለዜጎች እኩል እድል መስጠት ነው፡፡ መንግሥት እኩል እድል ባልሰጠበት ሁኔታ የዜጎች እኩል ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ስለማይቻል ሁሉም…
