ዜናዎች

_G2A2038
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ላበረከቱት አስተዋጽኦ የምስጋና እና የሽኝት መረሃ ግብር አደረገ
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በእስካሁኑ ለተቋሙ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የምስጋና እና የሽኝት መረሃ ግብር አድርጓል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ በመረሃግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተቋሙ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ለሀገሪቱ ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ትልቅ አሻራ ማስቀመጣቸዉን ገልጸዋል፡፡ አገልግሎቱ በ2014 ዓ.ም እንደ አዲስ ሲመሰረት ከምንም በመነሳት ተቋም በሂደት ወደ ተደራጀ ተቋማዊ አሰራር እንዲሚራ በትጋትና በሀላፊነት በመስራት ትልቅ ዉጤት አምጥተዋል ብለዋል፡፡ በተለይም ደግሞ በተለያዩ ጊዜያት ሀገሪቱ በርካታ አጣብቂኝ ጉዳዮች ዉስጥ በገባችበት ወቅት ክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና ሀገራዊ አንድነትን ለማስጠበቅ በቀዳሚነት ተሰልፈዉ ሲሰሩ መቆየታቸዉን አቶ ከበደ  አስታዉሰዋል፡፡ ክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ በአመራር በቆዩባቸዉ ጊዜያት ስራ ወዳድና ለህዝብ ስራ ምቹ ሁኔታዎችን የማይፈልጉ በመሆኑ ለሌሎች በዓርያነት የሚጠቀሱ ቆራጥ አመራር መሆናቸዉን በመጥቀስ ስም ከፍ ያለ ምስጋናን አቅርበዋል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ በበኩላቸዉ፣ አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የሀገሪቱ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በመርህ ተከትሎ እንዲሰራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸዉን ተናግረው አምባሳደሩ በተቋሙ ስለነበራቸዉ ዉጤታማ ቆይታ በተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ስም በማመስገን መልካም ምኞታቸዉን ገልጸዋል፡፡