የኢትዮጵያ የህትመት ዘርፍ የለውጡ መንግሥት ትልቅ ትኩረት በመስጠት ሰፊ ሪፎርም ካደረገባቸው ዘርፎች አንዱ ነው።

መሳፍንት ተፈራ፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ እንደገለጹት የኢትዮጵያ የህትመት ዘርፍ የለውጡ መንግሥት ትልቅ ትኩረት በመስጠት ሰፊ ሪፎርም ካደረገባቸው ዘርፎች አንዱ ነው።

‎በተለይም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያጋጠመውን ተቋማዊ ውስንነቶች በመለየት ተገቢውን ምላሽ መስጠት የሪፎርሙ ተቀዳሚ እርምጃ ነበር። የይዘት ጥራትና ብዝሀነትን ማስፋት፣ ሚዲያውን በቴክኖሎጂ ማዘመን፣ ተደራሽነትና ስርጭትን ማሳደግ እንዲሁም ተገቢ አደረጃጀትና መዋቅር መፍጠር የሪፎርሙ ትግበራዎች ዋነኛ ማጠንጠኛዎች ነበሩ። ይህ የለውጡ መንግስት ስኬቶች ከዘርፉ ባለፈ የሀገሪቱን የወል ትርክት በመቅረጽ አይነተኛ ሚና ተጫውተዋል።

#PMOEthiopia

See less

Similar Posts