የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
“የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ጉዟችን አካል እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ እመርታ ትልቅ ማሳያ የሆነው የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ተመርቆ አገልግሎት ጀምሯል። ቁልፍ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን መሰል ፋብሪካዎች ግንባታ፣ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ በመላ ሀገሪቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በተግባር ያረጋገጠ ነው።
ፋብሪካው የዓለም ዓቀፍ ጥራትና ተወዳዳሪነት መስፈርቶችን የሚያሟሉ የሴራሚክ ምርቶችን የሚያቀርብ ሲሆን፣ ለምርቱ የሚያስፈልጉትን ጥሬ ዕቃዎች ከ80 በመቶ በላይ ከሀገር ውስጥ ዐቅም ያገኛል። ይህ ስኬት ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሀብትና እምቅ ጸጋ የመጠቀም ብቃቷን ከመገንባቱ ባሻገር፣ ከውጭ ገቢ ምርቶች ላይ ያለንን ጥገኝነት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሰዋል።”
#MadeInEthiopia#EthiopiaDelivers
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication
See less
















