የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
“በያቤሎ ከተማ የሚገኘው የቦረና ባሕል ማዕከል ዛሬ ተመርቋል።
በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ2013 ዓ.ም የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለት የነበረውና ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የባህል ማዕከል፤ በመደመር መጽሐፍ ሽያጭ የተገነባ ሲሆን በ57.6 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው።
ማዕከሉ የገዳን ሥርዓት ለማሳየት በልዩ ሁኔታ ዲዛይን የተደረገ ሲሆን በአንድ ጊዜ እስከ 2000 ሰዎች ማስተናገድ አቅም ያለው የስብሰባ አዳራሽ እና የቅርስ ሙዚየምን አካቶ የተገነባ ነው። ማዕከሉ የቦረናን ህዝብ ባሕል፣ ታሪክ እና ፍልስፍና ለትውልድ የማሸጋገር ቁልፍ ሚና ይኖረዋል።”
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication
See less













