የጽናት ቀን
“ኢትዮጵያን ስናስብ፣ ሌት ተቀን በጽናት በመቆም ሀገርን ከጠላት ለመጠበቅ ወጥተው ለሚያድሩት ብርቱ የፀጥታ ኃይሎቻችን ቅድሚያ ሳንሰጥ ስለ ሁለንተናዊ ከፍታ ማሰብ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ለዚህም ነው በዚህ የጽናት ቀን፣ ለሀገረ-መንግሥታችን ዘላቂነትና ሉዓላዊነት ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የከፈሉትን የጀግኖቻችንን ታሪካዊ መስዋዕትነት በከፍተኛ ሀገራዊ ክብር የምንዘክረው፡፡
ዛሬ ላይ ሀገራችን በራሷ ዕውቀትና በልጆቿ አቅም የላቀ የቴክኖሎጂ ብቃት ያላቸውን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን፣ ዘመናዊ የታጠቁ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን፣ ከባድ መሣሪያዎችንና መድፎችን፣ እንዲሁም ተተኳሽ ጥይቶችን በራሷ ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎች ማምረት ችላለች፡፡ ይህ በራስ የመቆም አቅም፣ የሕዝባችን ሰላምና የሁለንተናዊ ኢኮኖሚ እድገታችን ጽኑ መሠረት በመሆኑ፣ ሀገራዊ ጽናታችንን በተጨባጭ ልማትና በጠንካራ የመጠበቅና የመከላከል አቅም እያረጋገጥን የኢትዮጵያን ዘላቂ ብልጽግና እናጸናለን!” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

