የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
“የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር እና ልዑካቸውን ዛሬ አግኝቻለሁ።
በቆይታችን በኢትዮጵያ እና በሕንድ መካከል ያለውን ጠንካራና የቆየ ወዳጅነት በድጋሚ ያረጋገጠ ሲሆን፤ ከሰሞኑ በሕንድ ካደረግኩት ጉብኝት እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ከነበረኝ ቆይታ ተከትሎ በተጠናከረ ትብብርና በስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ የተመሰረተ ወዳጅነታችንን ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ ተነጋግረናል።”
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication



