አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያን በተመለከተ
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ100 ሚሊዮን በላይ ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን፤ ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ በቻ ሳይሆን ትልቁ የአውሮፕላን ማረፊያ ባለቤት ያደርገዋል። ለዚህ ግዙፍ የ10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንትም ኢትዮጵያን በቀጣይነት የአፍሪካ የአቬሽን ማእከል ሆና እንድትቀጥል ያደርጋታል።
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ100 ሚሊዮን በላይ ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን፤ ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ በቻ ሳይሆን ትልቁ የአውሮፕላን ማረፊያ ባለቤት ያደርገዋል። ለዚህ ግዙፍ የ10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንትም ኢትዮጵያን በቀጣይነት የአፍሪካ የአቬሽን ማእከል ሆና እንድትቀጥል ያደርጋታል።
Office of the Prime Minister-Ethiopia
የኢፌድሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ግንቦት 14/2018 ዓ.ም መገናኛ ብዙኃን የዲሞክራሲ ሥርዐት ግንባታ አስቻይ መሠረተ ልማት ናቸው፡፡ መገናኛ ብዙኃን በሚዛናዊነት እና ገለልተኛነት የማገልገል ኃላፊነት ያለባቸዉ የዴሞክራሲ ተቋማት ናቸው፡፡ ኢትዮጵያም ይህንን መርሕ በሕገ መንግሥቷ ያረጋገጠች ሀገር ናት፡፡ ይህ ማለት ግን መገናኛ ብዙኃን የሚሠሩበት ሀገር እና የሚያገለግሉት ሕዝብ ብሔራዊ ጥቅም አይመለከታቸዉም ማለት አይደለም፡፡ ገለልተኛነታቸዉ ሕጋዊ አሠራርን ከመጠበቅ፣ ለአንድ…
“ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን ጋር ቀጣናችንን መልክ በሚያሲዙ እና የጋራ መፃኢ የልማት ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል። የሁለቱን ሀገሮች በላቀ እድገትና ተጠቃሚነት ዙሪያ መረጃ የተለዋወጥነ ሲሆን፤ የኢኮኖሚ ትስስርን በጠንካራ ትብብር እና በኢንቨስትመንት በመደገፍ እድሎችን የምናሰፋባቸውን የቀጣይ ስራዎች የተመለከተ ፍሬያማ ምክክር አድርገናል።” ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication Post Views: 55
የኮይሻ ፕሮጀክት ከኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት ባሻገር የቱሪዝም መስህብ የሚሆኑ ገፅታዎች እንዳሉት የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘የሚኒስትሮች ምክር ቤት ምልከታ በኮይሻ’ በሚል በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መንግስት በለውጡ የታደገው ሌላው ፕሮጀክት የኮይሻን ፕሮጀክት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የዱር እንስሳት መገኛ የሆነው እና አረንጓዴ የለበሰውን የጨበራ ጩርጩራ ለምለም…
“ዛሬ ጠዋት ከፕሬዝደንት ኡመር ጌሌህ የተላከ መልዕክት በመያዝ የመጡትን የጂቡቲ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና አለምአቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ኦማርን በጽሕፈት ቤታችን ተቀብያለሁ። በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ስላለው ትብብርም ተወያይተናል።” ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication Post Views: 48
የኢሚግሬሽና ዜግነት አገልግሎት ባለፉት ዓመታት ይስተዋሉበት የነበሩ የአገልግሎት ክፍተቶቹን ለማረም የተለያዩ የለውጥ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት ተቋሙ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙና ዲጅታላይዝ የሆኑ የፓስፖርት፤ የቪዛ፣ የትዉልደ ኢትዮጵያ መታወቂያ ፣የይለፍና የጉዞ ሰነዶች አገልግሎት፣ የውጪ ዜጎች አገልግሎት ፥ በአየርና በየብስ የድንበር ቁጥጥር አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል። ተቋሙ በአጠቃላይ የአገልግሎት አሰራሩን ይበልጥ በማዘመን ዜጎች የሚደሰቱበት ፥ተገልጋዮች…