የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
#ኢትዮጵያ
በአኒሜሽን ጥበብ፤
እጅግ ማራኪ ውበት፣ የማይደበዝዝ የታሪክ ትውፊት እና ድንቅ ብዝሃነት ያላት ምድር።
የሀገሬ ልጆች የኢትዮጵያን ድንቅ የብዝሃነት ውበት ትጎበኙ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ!
#ኢትዮጵያ
በአኒሜሽን ጥበብ፤
እጅግ ማራኪ ውበት፣ የማይደበዝዝ የታሪክ ትውፊት እና ድንቅ ብዝሃነት ያላት ምድር።
የሀገሬ ልጆች የኢትዮጵያን ድንቅ የብዝሃነት ውበት ትጎበኙ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ!
ዛሬ የCOP32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ ከCOP32 ሰብሳቢ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመሆን የአረንጓዴ ዐሻራ በአንድ ቀን 800 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ንቅናቄ ላይ የተሳተፉ ሲሆን፣ ይህም የአየር ንብረት መሪነት የሚጀምረው ተፈጥሮን በተግባር በመንከባከብ መሆኑን ጉልህ ማሳያ ነው። ለጽኑ አረንጓዴ ነገ፤ የተስፋ ዘሮችን በጋራ እየዘራን ነው! #አረንጓዴዐሻራ#COP32 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication Post Views: 25
“ታላቅ ወንድሜ እና ውድ ወዳጄ ክቡር ናሬንድራ ሞዲ፣ የዓለማችንን ትልቁን እና እጅግ ንቁ የሆነውን የዲሞክራሲ ማህበረሰብ ዘላቂ እምነት በማግኘት፣ ህንድን በራዕይ እና በቁርጠኝነት በተከታታይ ሶስት የዲሞክራሲያዊ የስልጣን ዘመናት በመምራት ላስመዘገቡት ታሪካዊ ስኬት የተሰማኝን ደስታ እገልጻለሁ። የእርሳቸው አመራር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ከድህነት ያወጣ፣ የዲጂታል ሕዝባዊ መሰረተ ልማትን በከፍተኛ ደረጃ ያስፋፋ እና ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ የመሰረተ…
“የአራት ዓመታት ተከታታይ ጥረት እና የሚጨበጥ ውጤት! በዘንድሮው “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖ ላይ የሀገራዊ ርዕያችንን ተጨባጭ ስኬት መመልከት ትልቅ ክብር ነው። ውጤት ተኮር አመራራችን ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ የኢንዱስትሪ መስፋፋት ተንጸባርቋል። ይኸውም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ በማድረግ፣ ባለፉት አራት አመታት ከ2,800 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ…
የአፍሪካ ኅብረት እና የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድኖች የኢትዮጵያን 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አዎንታዊና ሕጋዊ ማዕቀፉን የተከተለ እንደነበር በመግለፅ ፤ መንግሥት ዴሞክራሲን ለማጎልበት የሰራውን ሥራ አበረታተዋል ። በቀጣይም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ቅሬታዎቻቸውን በሕጋዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ፣ የሴቶች ተሳትፎና የውይይት ባህል ይበልጥ እንዲጎለብት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያውያን የውስጥ ጉዳያቸውን በራሳቸው እንዲወስኑ ዕድል እንዲሰጥ አሳስበዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች…
“የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ ለሶስተኛ ጊዜ የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው እንኳን ደስ አለዎት እያልኩ የተሰማኝን ደስታ እገልጣለሁ። የባርቤዶስ ሕዝብ ላደረገው ስኬታማ የዴሞክራሲ ልምምድ እያደነኩ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞትሊ ለባርባዶስ ሕዝብ እድገት፣ ብልጽግና እና ዘላቂ ልማት ለሚያደርጉት ጥረት መልካም እድል እንዲገጥምዎ እመኛለሁ። በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጠንካራ ትስስር እና ትብብራችንን ለማጠናከር በጋራ እንሰራለን።” ለተጨማሪ የመረጃ…
Post Views: 53
