የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም መካሄድ ጀምሯል

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀችው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ፡፡

የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም “ዘላቂ የከተሞች ልማት ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ 2063” በሚል መሪ ሀሳብ በአድዋ ሙዚየም መካሄድ ጀምሯል፡፡

በፎረሙ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ከ47 በላይ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ ተመራማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚካሄደው አህጉራዊ ፎረም የኢትዮጵያ ከተሞች ተሞክሯቸውን በማጋራት ከአቻ የአፍሪካ ከተሞች የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት ይሆናል።

Similar Posts