የሰላም አማራጭን በተመለከተ ።
በሀገራችን በመንግሥት ምህረትና ይቅርታ ተጠቅመው በየቀኑ በሺህ የሚቆጠሩ ኃይሎች የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ ይገኛሉ። ነገር ግን የኢትዮጵያ ዕድገትና ፍጥነት የሚያሰጋቸው አካላት አሁንም ተላላኪዎችን በመጠቀም እዚህም እዚያም ለመረበሽ እየሞከሩ ቢሆንም፣ በየትኛውም አካባቢ በትጥቅ ትግል የሚሳካና የሚመለስ ጥያቄ የለም። በመሳሪያ ትግል መንግሥትን መጣል በፍፁም የማይሳካ ‘ቅዠት’ መሆኑን በመገንዘብ፣ የሰው መሳሪያና የጠላቶች መገልገያ በመሆን የገዛ ወንድሞቻችሁን ከማጥፋት ወጥታችሁ በሰላማዊ መንገድ በመግባት አብራችሁን ለሀገራችሁ መልካም አስተዋጽኦ እንድትሰሩ ጥሪ አቀርባለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

