የቤት ልማትን በተመለከተ

መንግሥታችን የዜጎችን የቤት ፍላጎት ለመመለስ በከፍተኛ ትኩረት እየሰራ ይገኛል። በጉባ ብስራት ይፋ ያደረግነውን 1.5 ሚሊየን ቤቶችን የመገንባት ውጥን ለማሳካት የቤቶች ፖሊሲ፣ የሞርጌጅ ስርዓት፣ የመሬት እና የቴክኖሎጂ ዝግጅቶችን አድርገናል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ከተለያዩ ሀገራት በማስገባት በገጠርና በከተማ ሰፋፊ ግንባታዎችን እያካሄድን ነው። የቤት ግንባታ ስራው ከፍተኛ ግብአት፣ ልምድና እውቀት የሚጠይቅ ቢሆንም፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ከባንኮች ጋር በማስተሳሰር እየሰሩ ብድራቸውን የሚከፍሉበትን ስርዓት በቅርቡ እናጠናቅቃለን፤ ከባድ የሆነውን የ1.5 ሚሊየን ቤቶች እቅድ ለማሳካትም አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ እያደረግን እንገኛለን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Similar Posts