የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 49ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።
ምክር ቤቱ ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች፡- 1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ነው፡፡ ኮሚሽኑ ሀገራችን የኒውክለር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ መንገድ ከዓለም አቀፍ ማዕቀፎች ጋር በተጣጣመ መልኩ በኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በምግብ ዋስትና፣ በጤና አገልግሎት፣ በሳይንስ እና ምርምር ዘርፎች ላይ ለመጠቀም የምታደርገውን ጥረት የመምራትና…
