በፈጣን አፈጻጸም ተገንብቶ የተጠናቀቀውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን ለሕዝብ አገልግሎት እንካችሁ ብለናል!
ለዜጎቻችን ጤና እና ለከተማችን ዕድገት ያለንን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠው ይህ ስራ፤ ከፕሮጀክት የተሻገረ፣ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ እውነተኛ ገጽታ ነው! ለሁሉም ዜጋ የተገነባው ይህ ማዕከል የሚከተሉትን አካቷል፦ • 5.7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት እና የአረንጓዴ መዝናኛ ስፍራ፤ • የቀጣዩን ትውልድ ለማነቃቃት በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ የ15 አትሌቶቻችን የክብር ሐውልቶች፤ •…
