“በጂኦ ፖለቲካ ውጥረት እና በኢ-ተገማች ዲፕሎማሲ በሚስተዋልበት ሁኔታ በሀገራችን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ ችለናል” አቶ አደም ፋራህ
በጂኦ ፖለቲካዊ ውጥረት፣ በኢ-ተገማች የታሪፍ ዲፕሎማሲ፣ በአቅርቦት ሠንሰለት መቆራረጥ ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢኮኖሚ ዕድገት መቀዛቀዝ፣ የተዳከመ የማክሮ ኢክኖሚ ዓውድ በሚስተዋልበት ሁኔታ፣ በሀገራችን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ማስቀጠል መቻሉን በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ ክቡር አቶ አደም ፍራህ ገለጹ። ለዚህ አመርቂ ውጤት መመዝገብ ያበቃን የሦስት ዋና ጉዳዮች ድምር ውጤት ነው ያሉት አቶ…
