የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

ዛሬ ጠዋት ጂቡቲ ስደርስ ክቡር ፕሬዝደንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ አቀባበል አድርገውልኛል። ውይይታችን በጆኦፖለቲካል ጉዳዮች፣ በቀጠናዊ ሰላም እና ፀጥታ ብሎም የሁለትዮሽ ትብብራችንን በተለይም በንግድ፣ ሎጂስቲክስ እና የልማት ሥራዎች በምናጠናክርበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር። ይኽም ለሰላም እና መረጋጋት፣ የኢኮኖሚ ትስስር እና የጋራ ብልጽግና ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያመለክት ነው። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮችhttps://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቢሾፍቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ ያደረጉት ንግግር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቢሾፍቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ ያደረጉት ንግግር

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

ኢትዮጵያ እምቅ አቅሟን እና ታላቅ ርዕይዋን የሚመጥን ሌላ ተጨማሪ ሜጋ ፕሮጀክት ጀምራለች።

የቢሾፍቱ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የአውሮፕላን ማረፊያውን ግንባታ ይፋዊ በሆነ መርሃ ግብር ዛሬ በስፍራው አስጀምረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው እለቱ ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊነት እና ብልጽግና የምታደርገው ጉዞ አንድ እጥፋት ነው በማለት ገልጸውታል። የኢትዮጵያ…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ80 አመት አፍላ ወጣት ነው

መቀመጫው የአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአመት 25 ሚሊዮን ተጓዦችን በማስተናገድ በእጅጉ ተጨናንቋል። በ160 በላይ ዘመናዊ አውሮፕላኖች (በቅርቡ 60 አዲስ አውሮፕላኖች ይጨመራሉ) ወደ 145 በላይ መዳረሻዎች መብረር ሲታሰብ አንድ አውሮፕላን ጣቢያ እንደማይበቃ ግልጽ ይሆናል። ስለዚህም ተጨማሪ ማረፊያ መሥራት ይገባል። ትልቅ ታሪክ። የላቀ ትስስር። የላቀ እቅድ። PMOEthiopia ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮችhttps://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

ኢትዮጵያ ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ704.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ችላለች

ኢትዮጵያ ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ704.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ችላለች

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጥር 1 /2018 ዓ.ም ባለፉት ስድስት ወራት እንደ ሀገር በተከናወነ የተቀናጀ ሥራ ከ704 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል ። የገቢዎች ሚንስቴር የ6 ወራት የገቢ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያመላክተው ኢትዮጵያ በስድስት ወራት መሰብሰብ የቻለችው ከ704.4 ቢሊዮን ብር የሚልቅ ገቢ ባለፉት ጊዜያት ለዓመታት ሲሰበሰብ ከነበረው ገቢ የሚተካከል ነው ። መንግሥት የሀገር ኢኮኖሚ ዕድገትን…

ሁለንተናዊ ትብብር የኢትዮ-ቻይና አጋርነት የጀርባ አጥንት ነው

የኢትዮ-ቻይና የንግድ ልዉዉጡ ከ13 ቢሊዮን ዶላር በልጧል ። የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ታኅሳስ 30/2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለው የኢኮኖሚ ትብብር ቀጣይነት ባለው መልኩ እያደገ በመምጣቱ በሁሉቱ ሀገራት ያለዉን የንግድና ኢንቨስትመንት ፍሰትን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲስፋፋ አድርጓል፡፡ በዚህም የሁለትዮሽ የንግድ ለዉዉጥ ከ13 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የበለጠ ሲሆን፣ ይህም ቻይና ኢትዮጵያን ዋንኛ የንግድ አጋር በማድርግ ግንኙነቷን…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“ኢትዮጵያ እና ቻይና ለአስርት አመታት የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት አላቸው። ይኽ ግንኙነት በቅርቡ ወደ በሁኔታዎች የማይለዋወጥ የስትራቴጂክ ትብብር አድጓል። ዛሬ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን ተቀብዬ በጽናት በሚጓዘው የኢትዮጵያ እና ቻይና የመንግሥት እና ሕዝብ ግንኙነት ላይ ተነጋግረናል። በተለያዩ የልማት ትብብር ርዕሰ ጉዳዮችን ለማከናወን ያለንን ጽኑ አቋም በማስቀጠል ላይ ውይይት አድርገናል። በኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ መሠረተ ልማት፣ የኃይል…