የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት እና አንድምታዉ

“ከአንበሶች ግዛት እስከ አንበሶች ምድር” የጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ታሪካዊ የፓርላማ ንግግር” ኢትዮጵያና ሕንድ እንደ ሀገር ግንኙነት ከመሰረቱበት ጊዜ ጀምሮ በንግድ፣ በልማት እና በባህል ልውውጥ ዘርፎች ላይ በመተባበር ጥብቅ ወዳጃዊ ግንኙነት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ሁለቱ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን እና የደህንነት ጉዳዮችን ጨምሮ በአለም አቀፍ መድረኮች ላይ አንዳቸው የሌላውን ጥቅም ሲደግፉም ቆይተዋል። በኢትዮጵያና በሕንድ መካከል እየዳበረ የመጣው…

ኢትዮጵያዊያን ለሰላም፣ ለልማትና ዲሞክራሲ በአንድነት የሚነሱበት ትክክለኛ የከፍታ ጊዜ አሁን ነዉ – የሕንድ ሪፓብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ

ታኅሳስ 8/2018 ዓ.ም ኢትዮጵያዊያን ለሰላም፣ ለልማትና ዲሞክራሲ በአንድነት የሚነሱበት ትክክለኛ የከፍታ ጊዜ አሁን ነዉ – የሕንድ ሪፓብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ታኅሳስ 8/2018 ዓ.ም የሕንድ ሪብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ባደረጉት ንግግር፣ ጊዜዉ ትክክለኛ የኢትዮጵያ ከፍታ በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን ለሰላም፣ ለልማትና…

ኢትዮጵያ ከሰው ልጅ ታሪክ የጥንታዊ ሥልጣኔ መነሻዎች አንዷ ናት

“ኢትዮጵያ ከሰው ልጅ ታሪክ የጥንታዊ ሥልጣኔ መነሻዎች አንዷ ናት። በተራሮች፣ ሸለቆዎችና በኢትዮጵያውያን ልብ ታሪክ አለ” ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

ለ ሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የተደረገ የእራት ግብዣ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያደረጉት ንግግር :-

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

አዲስ ምዕራፍ መከፈቱን የሚያመለክት ታሪካዊ እጥፋት

“ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ኢትዮጵያን በመጎብኘትዎ እና የኢትዮጵያ እና ህንድን ግንኙነቶች እንዲጠናከሩ ለሚያደርጉት ጥረት ምስጋና አቀርባለሁ። ትስስራችንን ወደ ስትራቴጂያዊ ደረጃ ከፍ ለማድረግ የተወሰነው ውሳኔም በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ትብብራችንን ለማላቅ እና የጋራ እድገትን ለመተለም አዲስ ምዕራፍ መከፈቱን የሚያመለክት ታሪካዊ እጥፋት ነው።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

የኢትዮጵያና ህንድ የስትራቴጂካዊ አጋርነት አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ!

ይህ ጉብኝት በብሔራዊ ቤተመንግሥት ከተደረገው ደማቅ አቀባበል ባለፈ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን “የተሰሚነት ቁመት” እና ሕንድ ለአፍሪካ ቀንድ የምትሰጠውን “ስትራቴጂካዊ ክብደት” የሚያሳይ ነው። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የዳታ ማዕከል (Data Centre) ለመመሥረት የተደረገው ስምምነት ለኢትዮጵያ እጅግ ከፍተኛ ትርጉም አለው። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ መረጃዎቿን በዘመናዊ መንገድ ለማደራጀትና የሳይበር ደህንነቷን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት ሕንድ በቴክኖሎጂ…

የዲፕሎማሲ እና ታላቅነት ምሽት

ለጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን መዐከል የተደረገ የክብር ግብዣ። A night of diplomacy and grandeur State Banquet honoring Prime Minister Narendra Modi held at the Addis International Convention Center. #PMOEthiopia

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“ለህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይፋዊ አቀባበል ሥነሥርዓት አድርገናል። ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት ካደረግን በኋላ ከልዑካን ቡድኖቻችን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል። በውይይታችን በኢትዮጵያ እና ህንድ መካከል እያደገ የመጣውን ትብብር እና የወል ቅድሚያዎች የሚያንፀባርቁ አዳዲስ የትብብር መስኮችን ቃኘተናል። በሁለቱ ሀገራት መካከል በጉምሩክ የጋራ አስተዳደር ድጋፍ፣ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳታ ማዕከል ምስረታ የመግባቢያ…