የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ላበረከቱት አስተዋጽኦ የምስጋና እና የሽኝት መረሃ ግብር አደረገ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በእስካሁኑ ለተቋሙ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የምስጋና እና የሽኝት መረሃ ግብር አድርጓል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ በመረሃግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተቋሙ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ለሀገሪቱ ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ትልቅ አሻራ ማስቀመጣቸዉን ገልጸዋል፡፡ አገልግሎቱ በ2014 ዓ.ም እንደ አዲስ ሲመሰረት ከምንም በመነሳት…

ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ  አሕመድአራተኛውን “የመደመር መንግስት”  የተሰኘዉን መጽሐፍ አስመረቁ

መስከረም 6/2017 ዓ.ም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  አሕመድ አራተኛውን “የመደመር መንግስት”  የተሰኘዉን መጽሐፍ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬክሽን ማዕከል በትላንትናው ዕለት በይፋ አስመርቀዋል፡፡ አድሱ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ብልጽግና ጉዞ ዉስጥ የተገኙ ሁሉ አቀፍ ዉጤቶችና ተግዳሮቶች፣ እድሎችና ስጋቶች፣ እንዲሁም ተጨባጭ መፍትሔዎችን በማቅረብ የመደመር ፍልስፍናን በጥልቀት የሚተነትን ነዉ፡፡ በተለይም መጽሐፉ በዲጂታል ኢትዮጵያ የታገዘ ቀልጣፋ የህዝብ አስተዳደር ገጽታ፣ ሀገራዊ አንድነት እና…

ኢትዮጵያ ለማንሰራራት የሚስችላትን ከፍታ ይዛለች!

ኢትዮጵያ በሚመጥናት ከፍታ ልክ የሚያስቀምጣትን የማንሰራራት ጉዞ ጀምራለች፡፡ በጊዜ ምሕዋር ውስጥ ሲያጋጥሟት የነበሩ አንጋዳዎችን በብስለት እየተሻገረች ከፍታዋን በመያዝ ላይ ናት፡፡ የአይችሉም ትርክትን በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሰብራለች፤ ብርሃንን ለምሥራቅ አፍሪካ ፈንጥቃለች፡፡ ያለማንም ዕርዳታ በኢትዮጵያውያን ሀብት፣ ድካም፣ ዕውቀትና ጥረት ሕዳሴን በማጠናቀቅ ኢንዱስትሪዎቿን በበቂ ታዳሽ ኃይል የምታንቀሳቀስ፣ ከዚያም አልፎ ለጎረቤት አገራት የምታጋራ ኾናለች፡፡ በውኃ ሀብቶቿ በፍትሐዊነት በመጠቀም ዐዲስ…

ኢትዮጵያ የምታስተናግደዉ 2ኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባዔ ሀገራችን ያሳካቻቸው ተጨባጭ ልምዶችን የምታካፍልበት መድረክ ነው፡:

********************************* 2ኛዉ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ይህንን ጉባኤ የምታስተናግደዉ ለተሳታፊዎች ተጨባጭ ልምዶችን በማካፈል ጭምር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት ብቻ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እየሠራች ትገኛለች፡፡ መላዉ ኢትዮጵያውያን በተከታታይ ዓመት በሚያደርጉት የላቀ ተሳትፎ የራሳቸዉን ክብረ ወሰን እያሻሻሉ በአንድ ጀምበር ከ700 ሚሊዮን በላይ…

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ያላት ብዝኃነት ልዩ ዐቅም የሚፈጥርላት መሆኑ ተገለፀ።

“ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ መልእክት የኅብር ቀን በመላዉ ኢትዮጵያ እየተከበረ ነው፡፡ ብዝኃነትንና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በጠንካራ መሠረት ላይ ለመገንባት የሚያስችል፣ ብዝኃነት ለኢትዮጵያ ያበረከተዉን ፋይዳ እና በቀጣይም በላቀ ደረጃ እንዴት መጠቀም እንደሚገባ የሚያስገነዘብ የፓናል ውይይት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ጥንታዊና ገናና ታሪክ…

“ብዝኃነት ዐቅም፣ ውበት እና ጌጥ ነው፡፡” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

“ብዝኃነት ዐቅም፣ ውበት እና ጌጥ ነው፤ በዚያዉ ልክ ልንጠቀምበት ይገባል” ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ አስገነዘቡ፡፡ “ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ መልእክት የኅብር ቀን በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተከብሯል፡፡ በመድረኩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት ክቡር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ብዝኃነት የተሰናሰነ ዐቅም መኾኑን በመረዳት የማንነት፣ የሐሳብ፣ የታሪክ፣ የባህል እና የመሳሰሉትን ብዝኃነቶች የሚያስተናግድ ሥርዐት እየዳበረ እንደሚገኝ…

ፈታናዎችን በመገንዘብና የመሻገሪያ መንገዶችን ለመተለም ዜጎች ምንጊዜም ንቁ መሆን አለባቸዉ- ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

በመጪዉ ዓመት የሚኖሩ ፈታናዎችን አስቀድሞ በመገንዘብና የመሻገሪያ መንገዶችን ለመተለም ዜጎች ምንጊዜም ንቁ መሆን አለባቸዉ ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ የዘንድሮ የጷጉሜን ቀናት ስያሜን ተንተርሶ በሀገራዊ ጉዳዮች  ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም የተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት ሀገሪቱ ዉስብስብ ችግሮችን በመሻገር በሁሉም ዘርፎች አኩሪና እምርታዊ ድሎች ያስመዘገበችበት ዓመት እንደ ነበር አስታዉሰዋል፡፡…

የተዋሐደች እና የበለጸገች አፍሪካን እውን ለማድረግ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት በአፍሪካ ሕዝቦች መካከል ድልድይ መገንባትና ትስስር ማጠናከር ላይ መሥራት አለባቸው፡- ዶ.ር ለገሠ ቱሉ

ቀን-21-12-2017 የአፍሪካ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የኅብረቱ አጀንዳ 2063 እንዲሳካ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ባህል ትስስር መጠናከር ላይ እንዲያተኩር የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ.ር) አሳሰቡ፡፡ 15ኛዉ የምሥራቅ አፍሪካ የኮሙኒኬሽን ማኅበር (East African Communication Association) ኮንፈረንስ አዲስ አበባ ላይ እየተካሄደ ነው፡፡ በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ.ር)…

የፕሬስ መግለጫ

ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ማሳያ ናቸው። ብዝኃነት እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት መገለጫዋ የኾነችው ኢትዮጵያ የክረምቱን መገባደድ የሚያበስሩ ትውፊቶች ባለቤት ናት። ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ ልጃገረዶች ወደ ዐደባባይ በመውጣት የሚያሰሟቸዉ ኅብረ ዝማሬዎች በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የክረምቱን መገባደድ፤ በየጋራ ሸንተረሩ የአበቦችን መፍካት፣ የምንጮችን መጥራት እና የቡቃያዎችን ማፍራት ያበስራሉ። ከእነዚህ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች መካከል ከነሐሴ…

በኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ የሚነቀሳቀሱ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭን እየተቀበሉ ነዉ!

መንግስት በተለያዩ ሀገሪቱ አካባቢዎች ተንቀሳቅሰዉ የህዝቡን ሰላም የሚያዉኩ አካላትን ለመቆጣጠር የሰላም አማራጮችን ሲከተል ቆይቷል፡፡በዚህም በርካታ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበልና የታህድሶ ስልጠና በመዉሰድ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡ ሰሞኑን በኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂ ዞን እና በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተሳሳተ ዓላማ ወደ ጫካ ገብተው የነበሩ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሚሆኑ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭ ተቀብለው ገብተዋል። በበርካታ የኦሮሚያ አካባቢዎች…