ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጅቡቲ ገቡ፤

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጅቡቲ መግባታቸውን አስመልክቶ በፕሬዚዳንት እስማኤል ዑመር ጌሌ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያና በጅቡቲ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ የጋራ ፕሮጀክት ይፋ የሚሆንበትን መድረክ በጋራ ይታደማሉ። #PMOEthiopia

ተናግሮ ማድረግ ፣ ቃል ገብቶ መፈጸም !

መስከረም 8 /2018 ዓ.ም የዘንድሮው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ተራ የቀን መቁጠሪያ ለውጥ ብቻ አይደለም። ሀገራችን አዲስ ገጽ ገልጣ አዲስ ታሪክ ጽፋለች፤ መርጣለች፣ መክራለች፣ አሸንፋለች፣ አንሰራርታለችም። ፈተናዎች ወደ ታላቅ ዕድል ተቀይረዋል። በጸኑ እና ዝቅ ብለው በሠሩ ልጆቿ ጥረት የዘመናት የአዙሪት ጥላ ላይመለስ ተገፏል፤ ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት ብቻ ለበርካታ አስርት ዓመታት ያላሳካናቸውን ድሎች ማሳካት ችለናል። ሩቅ…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን!‎‎ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ፤ እያንዳንዱ ተማሪ ለላቀ እውቀት በትጋትና ጉጉት ትምህርቱን እንዲከታተል፣ ለጥሩ ውጤት በጽናት እንዲተጋ፣ እንዲሁም የሀገራችንን የወደፊት ዕድል መቅረጽ በሚያስችሉ ክህሎቶች እንዲገነባ አበረታታለሁ።‎‎ ዛሬ እየተገበርነው ያለው በርካታ የልማት ሥራዎች የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው፣ የዚህ ቀጣይ…

የኢትዮጵያ ማንሰራራት የአፍሪካን ሕዳሴ ያበሰራል !!

መስከረም 5/ 2019 ዓ.ም ኢትዮጵያ አዲሱን ዓመት ብሔራዊ ጥቅሞቿን በማስቀደምና የአፍሪካውያን እውነተኛ ድምፅ በመሆን ጀምራዋለች። በዓለም አቀፍ ተለዋዋጭ የጂኦፖለቲካ ውጥረት ውስጥ ጽኑና ገለልተኛ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን በመከተል የብሪክስ አባል መሆን የቻለችው ኢትዮጵያ፣ በሕንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ መሪዎች ጉባኤ ላይ አህጉራዊ አርአያነቷንና ስትራቴጂካዊ ተሰሚነቷን በተግባር አስመስክራለች። “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ…

18ተኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ የሁለተኛ ቀናት ቆይታ፦

‎‎የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካቸው ከመስከረም 2 /2019ዓ.ም ጀምሮ በተካሔደው 18ተኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ መሳተፋቸው ይታወሳል፤ ‎‎ መስከረም 3 ቀን፣ 2019 ዓ.ም የጉባዔው ሁለተኛ ቀን ‘‘ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት’’ በሚል መሪ ቃል የብሪክስ አባል እና አጋር ሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች በተሳተፉበት የተካሔደ ሲሆን፣ ጥምረቱ 140…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“በ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ የነበረን ቆይታ ቅኝት፦ ‎አዲሱን ዓመት የጀመርነው ስትራቴጂካዊ ጥቅሞቻችን በተረጋገጡበት እና የአፍሪካ ድምፅ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ባለበት ታሪካዊ ስኬት ነው!” ‎

ብሪክስ ለኢትዮጵያ ያመጣው ድል ምንድነው?

የብሪክስ የኒው ዴልሂ የአቋም መግለጫ መልሱን ይዟል።‎‎➡ ይበልጥ ለመረዳት ሙሉ የአቋም መግለጫውን ያንብቡ፦ brics2026.gov.in/brics-document/‎‎#PMOEthiopia #EthiopiaDelivers ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮችhttps://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

“ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በብሪክስ ፕላስ መድረክ ለአፍሪካ ጠንካራ ውክልና እና የፋይናንስ ተደራሽነት ጥሪ አቀረቡ”

አባልና አጋር ሀገራትን ባሳተፈው የብሪክስ ፕላስ የምክክር መድረክ ላይ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጠንካራ የአፍሪካ ውክልና እንዲኖር፣ የፋይናንስ እና የገበያ ተደራሽነት ይበልጥ እንዲሰፋ እንዲሁም ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ትስስርን ለማሳደግ ተግባራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪ አቅርበዋል። ‎‎በዚህ አውድም፣ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ አድማሱን በመላው አፍሪካ እንዲያስፋፋ የባንኩን ቢሮ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ኢትዮጵያ በሙሉ አቅም ዝግጁ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትሩ…