የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም መስፈን በጋራ እንደሚሰሩ ተናገሩ
የአማራ ከልል መንግስትና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት የምክክር መድረክ ከትናንት ጥቅምት 16-17/2018 ዓ.ም ጀምሮ በባሕር ዳር ከተማ ተካሄድዋል፡፡ በኢትዮጵያ የዳበረ የዲሞክራሲ ሥርዓትን ለመገንባት እና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ሰላማዊ ግንኙነት ለመፍጠር፣ እንዲሁም በመከባበርና በመተባበር ላይ የተመሰረተ ጤናማ የፖለቲካ ፉክክር እንዲኖር የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ…
