ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ባህር ዳር ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እንዲሁም ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ጋር በመሆን ባህር ዳር ከተማ ገብተዋል። #PMOEthiopia ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

በአማራ ክልል የመሰረተ ልማት፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ዕድገትን በተግባር ያረጋገጡ ዐበይት የልማት ውጤቶችን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ካጋሩት::

ሙሉውን ሂደት ለመረዳት ምስሎቹን ይመልከቱ! #PMOEthiopia ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

ስንተባበር ምን ማድረግ እንደምንችል ደጋግመን ለዓለም ያሳየንበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዛሬም በድል ተጠናቋል።

ሀምሌ 27 /2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ የሚለው ስም በጋራ የመቻልና የጽኑ አቋም ተምሳሌት ነው። መንግሥት የሀገሪቱን ዘላቂ ጥቅም ለማረጋገጥ የሚያስፈልጉ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን ሲያስቀምጥ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብም ሀገራዊ ፍላጎቱን በጋራ ተነሣሽነት እውን የማድረግ የዘመናት ልምምድ አለው። በተለይም መንግሥት ለአረንጓዴ ልማትና ሀገራዊ ከፍታ ለሚያቀርበው ጥሪ ሕዝቡ በላቀ ተሳትፎ ምላሽ የመስጠት ቁርጠኝነቱ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አብነት የሚሆን ነው። መንግሥት በኢትዮጵያ…

እንኳን ደስ አለን! – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዛሬ ኢትዮጵያ ከ805 ሚሊዮን በላይ ችግኝ በመትከል ታላቅ ታሪክ መፃፏን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ አድርገዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

በጋራ ተስፋን በመትከል የዛሬን የአንድ ጀምበር #አረንጓዴዐሻራ ግብ ለማሳካት ወደፊት ቀጥለናል።

Onwards we go, embracing the #GreenLegacy goal upon us today as we plant collectively ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ ለኢትዮጵያ የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ ከሚከናወን ስነ-ምህዳራዊ ግዴታ በላይ ነው !

ሀምሌ 27/2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ምድር ላይ እየተከናወነ ያለው “የአረንጓዴ ዐሻራ” ንቅናቄ ቀደሞ እንደሚታሰበው በቀላሉ ዛፍ የመትከል አካባቢያዊ ዘመቻ ብቻ ሳይሆን፣ የሃገርን ህልውና በስነ-ምህዳራዊ መሰረት ላይ እንደገና የመገንባትና የትውልድን እጣፈንታ የማደስ ታላቅ ስትራቴጂካዊ ሽግግር ነው። ይህ ጥረት የተሸረሸረውን የመሬት አካል መልሶ ከመጠገን አልፎ፣ በአየር ንብረት መዛባትና በተፈጥሮ ሃብት መናመን ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ቀድሞ…

ወደ #COP32 የሚያቀናው መንገድ በተግባር ላይ የተመሰረተ ነው!

‎‎ዛሬ የCOP32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ ከCOP32 ሰብሳቢ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመሆን የአረንጓዴ ዐሻራ በአንድ ቀን 800 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ንቅናቄ ላይ የተሳተፉ ሲሆን፣ ይህም የአየር ንብረት መሪነት የሚጀምረው ተፈጥሮን በተግባር በመንከባከብ መሆኑን ጉልህ ማሳያ ነው። ‎‎ለጽኑ አረንጓዴ ነገ፤ የተስፋ ዘሮችን በጋራ እየዘራን ነው! #አረንጓዴዐሻራ#COP32 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication