የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ዛሬ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ምክንያት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ የለም ብለዋል።
ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ በመግለጫቸው ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ተከታዩቹ ይገኙበታል። ማሻሻያው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ የሁለተኛው መካከለኛ ዘመን መርሃ ግብር ምሰሶ የሆኑ አራቱን መሰረታዊ ጉዳዮች ማለትም፦ 1) በሀገሪቱ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታን መፍጠር 2) የንግድ ስራዎችን የሚያሳልጡ የሚያቃልሉና ውጤታማነትን የሚያሻሽሉ የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢን ማሻሻል 3) የዘርፎቹች ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን የማሳደግ እና የመንግስት የማስፈጸም አቅምን…
