የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
”የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውና በማህበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የቀረቡበት የምክክር መድረክ ተገኝቼ ሃሳቤን አጋርቻለው። የማህበራዊ ዘርፍ ግንባታ እንደ ሌሎች መሠረተ-ልማቶች ውጤቱ ወዲያው የሚታይና የሚጨበጥ ባይሆንም፣ ለሀገር ዘላቂና ወሳኝ መሰረት የሚጥል ነው። ኢትዮጵያ በሚገጥሟት ተግዳሮቶች ሳትገደብ ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባች ሲሆን፣ ምንም እንኳ የዐቅም ውስንነቶች ቢኖሩብንም ለማሻሻል…

