የሚዲያ ኢንዱስትሪዉ ወደ ዲጂታል እንዲሸጋገር ድጋፍ እየተደረገ ነዉ
የሚዲያ እንዱስትሪዉ በሂደት ወደ ድጂታል እንዲሸጋገር በመንግስት ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በራሱ አቅም ያበለጸገውን የሞባይል መተግበሪያ (አፕ) በዛሬው ዕለት በይፋ አስመርቋል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የኢቢሲ የሞባይል መተግበሪያ ማስጀመሪያ ዝግጀት ላይ ተግኝተዉ ባስተላለፉት መልዕክት፣ መንግስት የሚዲያ እንዱስትሪዉን ዐጠቃላይ ወደ የዲጂታል ሽግግር…