18ተኛ የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን ውሎ

‎‎የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ‎በ18ተኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ሕንድ ኒው ዴልሂ አቅንተው፣ ዛሬ መስከረም 2 ቀን፣ 2019 ዓ.ም ‘‘ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት’’ በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ በዋለው የመሪዎች ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል። ‎‎ጉባኤው በመጀመሪያ ቀን ውሎ “አካታች ዓለም አቀፍ አስተዳደር እና ባለ ብዙ ወገን ትብብርን ማጠናከር” በሚል ዓቢይ ጉዳይ…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“ከብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን የቪየትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ሌ ሚን ሁንግን አግኝቸ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። በኢትዮጵያ እና ቪየትናም መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እና የጋራ ትብብራችንን ማስፋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረናል።”

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተን በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። ‎‎ውይይታችን በመከላከያ እና ደኅንነት፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኖሎጂ መስኮች ያለንን ትብብር ለማሳደግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጥንበት ነው። እንዲሁም የትምህርት ልምድ ልውውጦችን ማስፋት፣ በባህል እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ያለንን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“ከ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ከልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር መክረናል። ‎በቆይታችንም በዋና ዋና የብሪክስ ቅድመ-አጀንዳዎች እና በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ያለውን ሁለገብ ትብብር የበለጠ በሚያጠናክሩ ሂደቶች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።”

አዲስ ዓመትን በማስመልከት ማዕድ አጋርተዋልየጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የበዓል ማዕድ ማጋራትአዲስ ዓመትን በማስመልከት ማዕድ አጋርተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አዲስ ዓመትን በማስመልከት ማዕድ አጋርተዋል። ይህ መልካም እሴት በሰርክ እና እንዲህ ባለ የበዓላት ወቅት በሰፊው ባህል ሆኖ መቀጠሉ ከትላንት እስከ ዛሬ የኢትዮጵያውያን መገለጫ መሆኑን ማሳያ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ፣ አደረሰን!! “ዘመን ከፈጣሪ ለሰው የተሰጠ የመሥሪያ መጽሐፍ ነው። ይህ የመሥሪያ መጽሐፍ ለእያንዳንዱ ሰው የተሰጡ የተወሰኑ ገጾች አሉት። የመጨረሻው ገጽ ተጠናቅቆ የማጠቃለያው ሽፋን እስኪከደን ድረስ የፈለግነውን የመጻፍ መብት በእጃችን ነው። አንዳንዶች ዓለምን የቀየሩ ሐሳቦችንና ሥራዎችን፤ ሌሎች ታሪክን የቀየሩ ዕሳቤዎችንና ቴክኖሎጂዎችን ጽፈውበታል። በተቃራኒው ዓለምን ያወደሙ፤ ሕዝብ የከፋፈሉና የጨረሱ፤ ተፈጥሮን ያዛቡ፤ ክፋትንና ጭካኔን ያስተማሩ…

«ተስፋን እንትከል»

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር አብሮ በመሆን «ተስፋን እንትከል» በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረውን የዚህን ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያን በጋራ የችግኝ ተከላ በማካሄድ አከናውነዋል። ‎የ2018 ዓ.ም የችግኝ ተከላ መጠናቀቅን ስናበስር የተተከለው እያንዳንዱ ችግኝ የሕብረታችን፣ የሕዳሴያችንና የዘላቂ እድገታችን ሕያው ምልክት መሆኑን በማስታወስ ነው።‎ ‎በጽኑ አንድነታችንና በጋራ…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ጉዞ፡ በተግባር የታነጸበት ስራ “ዛሬ በሞጆ ተገኝተን ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬት ትልቅ ሚና የሚጫወተውንና በ60 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባውን ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማስፋፍያ የመጀመሪያ ምዕራፍ አስመርቀናል። ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በዓመት እስከ 1 ሚሊዮን ባለ 20 ጫማ ኮንቴነሮች የማስተናገድ አቅም ያላቸው ጣቢያዎችና ዘመናዊ መጋዘኖች ያሉት ሲሆን፣ የደረቅ…

የነገው ቀን

የነገው ቀን

“ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር ከወረቀት ወደ ዲጂታል፤ ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! ትናንትን በመማርና በማረም ዛሬን በላቀ ትጋት በመገንባት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የዕለት ተዕለት ባህላችን እየሆነ ነው። ንግድና አገልግሎትን ያቀላጥፋል፣ መረጃዎችን ተደራሽ ያደርጋል፣ ዘርፎችንም ያዘምናል! የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደሮች ንቅናቄ ወጣቶችን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጣሪ በማድረግ ወደ 7 ሚሊዮን ግባችን እያመራ ሲሆን የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን አረጋግጧል። በሀገር በቀል…