የመደመር መጽሐፍት የሞባይል መተግበርያ
ማስጀመርያ መርሃ ግብር ላይ የተደረገ ውይይት። #PMOEthiopia
ማስጀመርያ መርሃ ግብር ላይ የተደረገ ውይይት። #PMOEthiopia
ፈጠራን መሰረተ ልማት ያደረገ እና በሁሉም መስክ ሉዓላዊ ኢትዮጵያን ለመፍጠር የተነደፈ ሀገራዊ ትልምና ራዕይ ነው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ታኅሳስ 14/2018 ዓ.ም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የሀገሪቱን የዲጂታል ሽግግርን በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በመንግሥት አሥተዳደር ማዕቀፍ ዉስጥ ለማካተትና በእስካሁኑ የተመዘገቡ የኢኮኖሚ ስኬቶችን ይበልጥ ለማጠናከር የተነደፈ ሀገራዊ ራዕይ ነዉ፡፡ ዕቅዱ ሁሉን አቀፍ እድገት እና ዓለም አቀፍ…
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጻፉት “መደመር” ፣ “የመደመር መንገድ”፣ “የመደመር ትውልድ” እና “የመደመር መንግሥት” መጻሕፍት ሰው ተኮር በሆነ የብዝሃ ኢኮኖሚ ጉዞ ኢትዮጵያን በአጠረ ጊዜ ውስጥ ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር አግዘዋል። በእነዚህ መጻሕፍት የተነሱ እሳቤዎች ከንድፈ ሃሳብ ባሻገር በተግባር የተገለጡና ለትውልዱ ብሩህ ተስፋን ያጎናጸፉ ናቸው። መጻሕፍቱ አሁን ከሕትመት ባሻገር በ Medemer መተግበሪያ አማካኝነት በድምጽ ተተርጉመው ቀርበዋል።…
ታኅሳስ 13/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ምክንያቱም ከሰላም የበለጠ ምንም ነገር የሌለ በመሆኑ፡፡ ሰላም ለሰው ልጅ እድገትም ሆነ ለሀገር ግንባታ ሂደት ዋንኛዉ መነሻ ነው፡፡ ሰሞኑን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የተደረጉ ሕዝባዊ ዉይይቶች የሕዝብ ድምጽ ጎልቶ እንዲሰማ ማድረጉንና ሕዝቡ ለዘላቂ ሰላምና ልማት ቁርጠኛ መሆኑን የታየበት ሁነኛ መድረክ ነበር፡፡ የዉይይቱ ተሳታፊዎች…
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ሁሉን አቀፍና አካታች የዲጂታል አገልግሎቶች የሚቀርቡበት፣ ዜጎችን ማዕከል ያደረገ ስርዓትን በመዘርጋት፣ ሉዓላዊና ደህንነቱ የተጠበቀ አውድን ለመፍጠር ቁልፍ ሚና ይኖረዋል።
#DigitalEthiopia2030 #PMOEthiopia
የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ መንደርደሪያ ያደረገዉ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025”ን ሲሆን በዋናነት ሦስት ግቦችን ለማሳካት ዓላማ ያደረገ ነዉ፡፡ አንደኛዉ ግብ ተደራሽነትን ማስፋት ሲሆን ይህም ሁሉም ዜጎች ከቤታቸዉ፣ ከስልኮቻቸዉ እና ካሉበት ስፍራ ሆኖ የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበትን እድል መፍጠር ነዉ፡፡ ሁለተኛዉ ግብ ለዜጎች እኩል እድል መስጠት ነው፡፡ መንግሥት እኩል እድል ባልሰጠበት ሁኔታ የዜጎች እኩል ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ስለማይቻል ሁሉም…
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ ሁለት መሠረታዊ አስቻይ ጉዳዮች አሉ። አንደኛው የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ነው። የኤሌክትሪክ ተደራሽነት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ምግብ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል። የምንጠቀምባቸው የቴክኖሎጂ ጋጄቶች ኤሌክትሪክ ይፈልጋሉ። በመሆኑም በሁሉም አማራጮች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ማስፋት አለብን። ሁለተኛው የኢንተርኔት ትስስር ነው። በርካታ ከተሞች የኢንተርኔት ትስስር ተጠቃሚ ሆነዋል። ነገር ግን በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ይህን ትስስር በሁሉም አካባቢዎች…
ኢትዮጵያ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቅ ፣ ዜጎችን ማዕከል በማድረግ ፍትሃዊ ተደራሽነት የሚያሰፋውን፣ በዜጎችና በተቋማት መካከል መተማመንን የሚያሰፋውን ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ ጀምራለች ። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication
“ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ላይ ቁልፍ ጉዳይ ሆኖ ተተግብሯል። አሁን ላይ 30 ሚሊዮን ዜጎች ፋይዳ መታወቂያ ተመዝግበዋል። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ላይም ፋይዳ ስትራቴጂካዊ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ተደራሽ የማድረግ ስራም ይሰራል። በተለይ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ያሉ አገልግሎቶችን ከፋይዳ ጋር በማስተሳሰር በስትራቴጂው የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት ይሰራል። ለዚህ ደግሞ ሁሉም በትብብር ሊሰራ ይገባል።”…