የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት
የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር፦ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስምንተኛ ዓመቱን በያዘበት በዚህ ዓመት፤ የኮፕ32 (COP32) ሰብሳቢ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የኮፕ32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ዓመታዊውንና የአንድ ጀምበር ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን መርተዋል። ዘመቻው በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአንድ ቀን ውስጥ 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታላቅ…
