መንግስት የኢኮኖሚ እድገቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥና የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ።
አዲስ አበባ፣ ጥር 10 ቀን 2017 ዓ.ም መንግስት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት ቀጣይነት ለማረጋገጥና የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ የኢፌድሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ሚንስትሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በመንግስት የተቀረጹ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎች የኢኮኖሚ እድገትን እዉን እንዲያደርግና የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ እንዲለዉጥ በሁሉም ዘርፎች እየተሰራ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ለገሰ…
