Similar Posts
በኃብት ስጦታ አንፃር ስንመለከት ኢትዮጵያ ለሁሉም የሚበቃ ኃብት እንዳላት እናውቃለን። በባሌ ዞን ከተለያዩ አመራሮች ጋር ያደረግነው ጉብኝት የመጨረሻ መዳረሻ አስደማሚው የፊንጫ ሀበራ ፏፏቴ ሆኗል። በግርማ የሚወርደው ፏፏቴ ወደ ሶፍኡመር የዋሻ ሥርዓት የሚደመረውን የወይብ ወንዝ የሚቀላቀል ነው። የኢትዮጵያ ቀይ ቀበሮ የሚገኝበት ይኽ አስደናቂ ከባቢ ድንቅ የአዕዋፍ መገኛና በቅርቡ የዋሻ መስህብ የተገኘበት እንዲሁም የራፉ ውብ የዐለት ደን አቅራብያ የሚገኝ ነው። በቅርቡ በአካባቢው የሚገነባው ማረፊያ ሲጠናቀቅም ለጎብኝዎች የበለጠ ሳቢ እና ምቹ ይሆናል።
ባለፉት ሶስት ቀናት በጉብኝቱ የተሳተፉ የቀድሞ እና በሥራ ላይ ያሉ ኃላፊዎች በጉብኝቱ የተመለከቱት የተፈጥሮ፣ የባሕል እና የሰው ኃብት ከፍ ያለ መነሳሳትን ፈጥሮላቸዋል። የጋራ ሥራችን እነዚህን ኃብቶቻችንን መግለጥ፣ ማሳደግ፣ በኃብቶቹ ላይ በመጨመር ቀጣዩ ትውልድ ችቦውን ተረክቦ እንዲቀጥል መሠረት መጣል ነው። ኢትዮጵያ በርግጥም የተትረፈረፈ ኃብት ምድር ናት። እንሰባሰብ። ለማለም እንድፈር። የጋራ ነጋችንን በጋራ እንገንባ። Gama qabeenyaatiin yoo…
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ! ዘንድሮ የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት የምናከብረው የተነገረው የተስፋ ቃል መድረሱን፣ የለውጥ ብርሃን መፈንጠቅ መጀመሩን፣ የመሻገር ዘመን መቅረቡን እያመንን ነው። ጉዟችን በውጣ ውረድ የተሞላ ነበር፤ ተስፋ አስቆራጭ መከራዎችን አስተናግደናል። ከእንግዲህ ፈተናው ጨርሶ አይጎበኘንም ባንልም፣ ተስፋችን የሚወለድበት የዋዜማው ዕለት ላይ ደርሰናል። የፍዳው ዘመን ላይመለስ ተሸኝቶ፣ የማንሠራራት ዘመን እንደመጣ በልበ ሙሉነት መናገር እንችላለን።…
መልካም የገና በዓል! ገጠራማ አካባቢዎችን ማሻገር አለብን
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተጨማሪ መረጃ👇https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication Post Views: 286
የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን እና የኢትዮጵያዊያንን ዉበት የሚያጎላ ነው፡
ኢትዮጵያ የብዝኃ ቋንቋ፣ ብዝኃ ባህልና ብዝኃ ማንነት ሃገር ናት፡፡ ብዝኃነት ለኢትዮጵያዊያን ተፈጥሯችን፣ ዉበታችንና የጥንካሬአችን ምንጭ ነው፡፡ ብዝኃ ማንነት ያለበት ሕዝቦች ሀገር መሆናችን ጸጋችን ነው፤ ብዝኃነት የኢትዮጵያ ተጨባጭ እዉነታና ውብትም ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ሂደት አንድ ጠንካራ ሀገር ለመገንባት በርካታ መንገዶች ተሞክሯል፡፡ ነባሩንና ተፈጥሯችን የሆነውን ብዝኃ ማንነትን በአንድ ወጥ ማንነት ለመቀየር ብዙ ተለፍቶበታል፡፡ በፖሊሲና ተቋማዊ አሰራር…
“አንድ ክር ደካማ ነው። ብዙ ክር ግን የማይበጠስ ገመድ ነው።“
“አንድ ክር ደካማ ነው። ብዙ ክር ግን የማይበጠስ ገመድ ነው። ስንበዛና ስንሰናሰል በቀላሉ የማንበጠስ ጠንካራ ገመድ ስለሆንን መተባበር፣ መከባበር፣ በጋራ መቆም፣ ብሄራዊ ጥቅምን ማስቀደም የሁላችንም ሃብትና ስንቅ እንዲሆን አደራ እላለሁ።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) Post Views: 142




















