የኢትዮጵያውያን 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር የመትከል ታሪካዊ ክንውን

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ፣ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታሪካዊው ሀገራዊ መርሐ ግብር ዛሬ በይፋ መጀመሩን አስታውቀዋል።

“ኑ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ያለው ይህ መርሐ ግብር፣ የተጎዳችውን ምድር ለማከምና ለቀጣዩ ትውልድ አረንጓዴ ዐሻራን ለማሳረፍ ያለመ መሆኑን ሚኒስትሯ በመግለጫቸው አብራርተዋል።

አክለውም፣ ኢትዮጵያውያን በመደመር ዕሳቤ በአንድነት ሆነው ለምድር የሚሰጡትን አደራ፣ መሬትም በተራዋ በእጥፍ እንደምትመልስ በማንሳት የሕዝቡን ተነሳሽነትና አኩሪ ባህል አውስተዋል።

በዘንድሮው የክረምት ወቅት በአጠቃላይ 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ከተያዘው ሀገራዊ ዕቅድ አካል የሆነው ይህ የዛሬው ታሪካዊ የችግኝ ተከላ፣ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች የነቃ ተሳትፎ በደማቅ ሁኔታ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts