በአንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ.ዴሌቦ ህልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለፁ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሰተላለፉት የሀዘን መግለጫ “አንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ላዺሶ ጌ. ዴሌቦ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ማለፋቸውን በታላቅ ኀዘን ሰማሁ። ነፍሳቸውን በዐጸደ ገነት እንዲያኖርልን እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንዲሰጥልን እመኛለሁ።” ብለዋል፡፡

በአንድ አመት ጊዜ ብቻ እነዚህን ጊዜ የማይገድባቸው ቋሚ ምስክሮች አዲስ ሕይወት የዘራበት እድሳት ተከናውኗል

እንደገና የፈካውን የጎንደር አብያተ መንግሥታት ዓለም አቀፍ ቅርስ ይመልከቱ፣ ታሪክ እና ጥበበ እድ የተገናኙበትን አስደናቂ የኢትዮጵያ የንጉሳዊያን ቅርስ የእድሳት መልክም ይጎብኙ። የተከናወነው እድሳት በአንድ አመት ጊዜ ብቻ እነዚህን ጊዜ የማይገድባቸው ቋሚ ምስክሮች አዲስ ሕይወት የዘራበት እድሳት ተከናውኗል። በጥንቃቄ ከታደሱት የታሪክ ሀብቶች መካከል 40,000 ስኴር ሜትር ላይ ባረፈ የአረንጓዴ ምድር ማስዋብ ሥራ የተከበቡት የአፄ ፋሲል፣ የአፄ…

“በባህር ዳር ከተማ በነበረን ጉብኝት የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን እንዲሁም ከተማዋን ለቱሪዝም ዘርፍ ምቹ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ተመልክተናል።”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በባህር ዳር ከተማ በነበረን ጉብኝት የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን እንዲሁም ከተማዋን ለቱሪዝም ዘርፍ ምቹ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ተመልክተናል። የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ባስቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ደረጃውን የማሻሻል ስራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ነው። ስታዲየሙ 52 ሺህ ተመልካቾችን መያዝ የሚችል ሲሆን የወንበር መግጠምና የሳር ንጣፍ…

“በጎርጎራ ጣናነሽ የተሰኘችዉን ጀልባ ሥራ አስጀምረናል”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በጎርጎራ ጣናነሽ የተሰኘችዉን ጀልባ ሥራ አስጀምረናል። በጣና ውሃ ላይ እየቀዘፈች ባሕር ዳር ከተማን ከጎርጎራ ኤኮ ሎጅ ማገናኘት ጀምራለች። ከ180 ተጓዦች በላይ የማጓጓዝ አቅም ያላት ጣናነሽ ለጉብኝት፣ ለመዝናናት እና አስደማሚውን የጣና ሀይቅ የተፈጥሮ ከባቢ ለመጎብኘት ወደ ጎርጎራ ኤኮ ሎጅ የሚደረገውን ጉዞ የበለጠ ምቹ አድርጋዋለች። In Gorgora, we’ve launched the voyage of…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እድሳት የተደረገለትን የፋሲል ግቢ በሚመርቁ ወቅት ያስተላለፉት መልዕክት:-

የጎንደር ህዝብ ታላቅ በሆነው በዚህ ደስታው ተካፋይ እንድንሆን ስለፈቀደልን እናመሰግናለን ። ጎንደር ሽማግሌዎች አሏት ባዕድ ሳይሆን ባላገሮች፣ ባለቤቶች እንኳን ከአንድ ሰፈር ወደ ሌላ ሰፈር ተንቀሳቅሰው የሀገራቸውን ልማት ማየት፣ ማገዝ እንዲችሉ ሰላም ያስፈልጋል ። የወጡ ወንድሞቻችን ጊዜ ማባከን የለባቸውም፤ የሚያስፈልገን ተመልሰው በአንድነት እና በትብብር መሥራት፣ ሀገር ማልማት አለብን ። ዛሬ ጎንደርን፣ ባሕርዳርን ወይም አማራ ክልልን ከአማራ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የታደሰውን የፋሲል ጊቢ መርቀዋል።

የተከናወነው ሰፊ የእድሳት ሥራ በቅርስ ስፍራው ነባሩን ታሪክ በመጠበቅ ውበቱን እና ተደራሽነቱን በማሻሻል አዲስ እስትንፋስ የሰጠ ሆኗል። የእድሳት ሥራው የቤተመንግሥቱን የግንባታ መዋቅር መጠገን፣ የእግር መንገዶችን ማሻሻል፣ ቁልፍ የሆኑ ሕንፃዎችን ከዝግባ እና ዋንዛ በባሕላዊ ቁሳቁሶችን ተጠቅሞ በማደስ የስፍራውን ግለ ወጥ መልክ እና ባሕርይ ለመጠበቅ ተሰርቷል። ለጎብኝዎች ምቾት የተሰናዱ አገልግሎት መስጫዎችም ትርጉም ባለው ደረጃ ተሻሽለዋል። አዲስ የቱሪስት…

“ጉልበት ይሸሻል፣ ጊዜ ይሸሻል፣ ስልጣን ይሸሻል፣ ሁሉ አላፊ ነው ፣ የማያልፈው እንደዚህ ያለው ታላቅ ስራ ነው።”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

“በጎንደር በነበረን ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ ገምግመናል”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በጎንደር በነበረን ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ ገምግመናል። ፕሮጀክቱ 870 ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን 17000 ሄክታር መሬት በመስኖ አቅርቦት ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል። የፕሮጀክቱ ቁልፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ መልኩ ተጠናቋል። የቀሩት ሥራዎችም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እየተካሄዱ ይገኛሉ። የመገጭ ግድብም በሚጠናቀቅበት ወቅት የአካባቢውን የግብርና ምርታማነት የሚያሳድግ ይሆናል። Daawwannaa…

በመገጭ የመስኖ ፕሮጀክት የፕሮጀክቱ ቁልፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ መልኩ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሙሉ መልዕክት :- “በጎንደር በነበረን ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ ገምግመናል። ፕሮጀክቱ 870 ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን 17000 ሄክታር መሬት በመስኖ አቅርቦት ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል። የፕሮጀክቱ ቁልፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ መልኩ ተጠናቋል። የቀሩት ሥራዎችም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እየተካሄዱ ይገኛሉ። የመገጭ ግድብም በሚጠናቀቅበት ወቅት የአካባቢውን የግብርና ምርታማነት…

ኢትዮጵያ የጂኦ-ቱሪዝም እምቅ ሀብቶቿን በዩኔስኮ በማስመዝገብ ተጠቃሚነቷን ለማሳደግ ተዘጋጅታልች

በኢትዮጵያ የጂኦ-ቱሪዝም እምቅ ሀብቶቿን በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ የጂኦ-ፓርክነት በማስመዝገብ ተጠቃሚነቷን ለማሳደግ የዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል ። ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላት ያልተነካ ሀብት በጂኦ-ቱሪዝም ተመራጭ ሀገር የሚያድርጋት ነው። ከዚህ አንጻር ለዩኔስኮ በወደፊቱ ሊቀርቡ የሚችሉ በርካታ የሀገሪቱ እጩ የጂኦ-ቅርስ ቦታዎች ተለይተዋል። ከነዚህም ውስጥ በባሌ ወረዳ የሚገኘው ሶፍ-ዑመር ዋሻ፣ በቡታጅራ-ስልጤ የሚገኙት አፈጣጠሮች፣ የሰሜንና የገራልታ ተራሮች፣ የደናክል ስምጥ ሸለቆ፣ ኤርታ…