በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተጀመረው የፍትህ አሰጣጥ ቴክኖሎጂ በሁሉም ክልሎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ ።

ኢሬቻ ኢትዮጵያ ለዓለም የምታበረክተዉ ድንቅ እሴቷ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ለዓለም አበርክታለች፡፡ እሴታቸዉን ጠብቀዉ ለዘመናት በሕዝብ እየተከበሩ የዘለቁ ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላትንና ትውፊቶቻቸዉን በተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ፣ የትምህርት እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የሰው ልጆች ሁሉ ሀብት ተብለው እንዲመዘገቡም አድርጋለች፡፡ ለምዝገባ በሂደት ላይ የሚገኙ በርካታ እሴቶች ባለቤትም ነች፡፡ ኢሬቻ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ በየዓመቱ የሚከበር የይቅርታ እና የምስጋና በዓል ነው፡፡…

መንግሥት ቃልን በተግባር በመግለጽ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ እያሳካ ነው!

*************************** መንግሥት ከለውጡ እውን መሆን ጀምሮ የገባቸዉን ቃሎች እየፈጸመ፣ ኢትዮጵያን ወደሚገባት ከፍታ ለማውጣት የብልጽግና ጉዞዉን እያሳመረ ቀጥሏል፡፡ ከዓመታት በፊት በ2018 ዓ.ም ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ብርሃን ሽግግር እናደርጋለን የሚል የሚል ርዕይ የያዘው ቃል የኢፌዴሪ መንግሥት ቃሉን በተግባር እየገለጸ ይገኛል፡፡ የምግብ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ ብዙ ርቀት ተጉዘናል፤ በመኸር እርሻ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በአረንጓዴ ዐሻራ እና በበጋ መስኖ በመታገዝ ሰፋፊ…

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለኢፌዴሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር የዕውቅና እና የምስጋና ስጦታ አበረከተ፡፡

መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ/ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለኢፌዴሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር በ2017 ዓ/ም ጉባኤው የሠራቸውን የሰላም እና ማሕበረሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎች ለሕዝብ በስፋት ተደራሽ ይሆኑ ዘንድ በቂ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ ላበረከተው ሁሉን አቀፍ አገልግሎት በዛሬው ዕለት የዕውቅና እና የምስጋና ስጦታ በክብር አበርክቷል፡፡ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸኃፊ ሊቀ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የኃይል ማመንጫ፣ ግብርና፣ የጤና ጥበቃ ልማት እና የመከላከያ ትብብርን ጨምሮ ሰፊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ውይይቱ ለማኅበረሰብ አገልግሎት የሚውል ንፁህ ኃይል ምንጭ የሚውል የጋራ የኒኩሊየር ኃይል ማመንጫ የማልማት ስምምነቶችን ጨምሮ የጋራ ፍላጎት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተካሂዷል። Prime Minister Abiy Ahmed held talks with President Vladimir Putin on a…

ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት የኢትዮጵያ ብዝኃነት ማሳያ ናቸው!

************************** የመስቀል ደመራ በዓል ኢትዮጵያ በዓለማቀፍ ደረጃ በማይዳሰስ ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው መካከል አንዱ ነው፡፡ በዓሉ በመላው ኢትዮጵያ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተወራረሰ እና ተጠብቆ የቀጠለ ክዋኔን የሚያሳይ የኢትዮጵያ ብዝኃነት እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ማሳያ ነው፡፡ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበዉም ይህንን ነባር የአከባበር ትውፊቱን ይዞ እንዲቀጥል፣ ከኢትዮጵያ አልፎ የሰው ልጆች ኹሉ…

ክብርት እናትዓለም መለሰ በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቀባበል ተደረገላቸው፡፡

መስከረም 09 ቀን 2018 ዓ.ም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር በመኾን የተሾሙት ክብርት እናትዓለም መለሰ ዛሬ በአገልግሎቱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ከአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋርም ትውውቅ አድርገዋል፡፡ *************

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ላበረከቱት አስተዋጽኦ የምስጋና እና የሽኝት መረሃ ግብር አደረገ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በእስካሁኑ ለተቋሙ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የምስጋና እና የሽኝት መረሃ ግብር አድርጓል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ በመረሃግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተቋሙ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ለሀገሪቱ ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ትልቅ አሻራ ማስቀመጣቸዉን ገልጸዋል፡፡ አገልግሎቱ በ2014 ዓ.ም እንደ አዲስ ሲመሰረት ከምንም በመነሳት…

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  አሕመድ (ዶር) አራተኛውን “የመደመር መንግስት”  የተሰኘዉን መጽሐፍ አስመረቁ

መስከረም 6/2017 ዓ.ም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  አሕመድ(ዶር) አራተኛውን “የመደመር መንግስት”  የተሰኘዉን መጽሐፍ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬክሽን ማዕከል በትላንትናው ዕለት በይፋ አስመርቀዋል፡፡ አድሱ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ብልጽግና ጉዞ ዉስጥ የተገኙ ሁሉ አቀፍ ዉጤቶችና ተግዳሮቶች፣ እድሎችና ስጋቶች፣ እንዲሁም ተጨባጭ መፍትሔዎችን በማቅረብ የመደመር ፍልስፍናን በጥልቀት የሚተነትን ነዉ፡፡ በተለይም መጽሐፉ በዲጂታል ኢትዮጵያ የታገዘ ቀልጣፋ የህዝብ አስተዳደር ገጽታ፣ ሀገራዊ አንድነት እና…

ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ነገዋን እየሠራች ነው!

ኢትዮጵያ ነገዋን ዛሬ ላይ ለመሥራት እያደረገች ያለውን ጥረት እና የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስተዋወቅ 5ኛዉን የጳጉሜን ቀን “የነገዉ ቀን” በሚል ስያሜ እና “ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ” በሚል መሪ መልእክት እያከበረች ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከራሷ ባሻገር የአፍሪካን ማንሰራራት ለማብሰር ዛሬ ላይ ነገዋን እየሠራች ነው፡፡ ለአምስተኛዉ የኢንዱስትሪ አቢዮት የሚመጥን ትውልድ መቅረጽን፣ ለኢንዱስትሪ ዕድገቱ የሚመጥን ታዳሻ ኃይል ማቅረብን፣ የዘመኑ ከተሞችን መፍጠርን፣…