“በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
|

“በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

<< ነሐሴ 17፣ 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር::በአንድ መንፈስ በመላው ኢትዮጵያ ዓሻራችንን እናኑር፡፡ አንድ ከሆን ከዚህም በላይ እንችላለን!አዋቂዎች ከ20 በላይ፣ ታዳጊወች ከ10 በላይ በመትከል ለሀገር ያለንን ፍቅር፣ ለትውልድ ያለንን ስጦታ በተገቢው ስፍራ እንግለጥ፡፡Hagayya 17/2016 guyyaa tokkotti biqilruuwwan miliyoona 600 dhaabuudhaan ashaaraa keenya haa keewwannu.Guutummaa Itoophiyaatti qalbii tokkoon ashaaraa keenya haa…

“የመገናኛ ብዙኃን የተረጂነት አስተሳሰብን በመለወጥ ዜጎች ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል ተረጂነት ሃገራዊ ክብርንም የሚነካ መሆኑን በማስረዳትና ግንዛቤ በመፍጠር በኩል ከፍተኛ ኃላፊነት ተጥሎባችኋል፡፡”

“የመገናኛ ብዙኃን የተረጂነት አስተሳሰብን በመለወጥ ዜጎች ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል ተረጂነት ሃገራዊ ክብርንም የሚነካ መሆኑን በማስረዳትና ግንዛቤ በመፍጠር በኩል ከፍተኛ ኃላፊነት ተጥሎባችኋል፡፡”

ሰላማዊት ካሳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ፖሊሲ ላይ ለሁለት ቀናት የተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ሚኒስትር ዴኤታዋ እንዳሉት የሰብአዊ ድጋፍ ጠባቂነት አመለካከትን መየቀር የመገናኛ ብዙኃንና የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ኃላፊነት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም፣ሐብት ያላት ሃገር ናት ያሉት ሰላማዊት ካሳ…

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ዛሬ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ምክንያት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ የለም ብለዋል።
|

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ዛሬ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ምክንያት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ የለም ብለዋል።

ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ በመግለጫቸው ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ተከታዩቹ ይገኙበታል። ማሻሻያው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ የሁለተኛው መካከለኛ ዘመን መርሃ ግብር ምሰሶ የሆኑ አራቱን መሰረታዊ ጉዳዮች ማለትም፦ 1) በሀገሪቱ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታን መፍጠር 2) የንግድ ስራዎችን የሚያሳልጡ የሚያቃልሉና ውጤታማነትን የሚያሻሽሉ የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢን ማሻሻል 3) የዘርፎቹች ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን የማሳደግ እና የመንግስት የማስፈጸም አቅምን…

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ38ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ38ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 38ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡38ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎችየሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 38ኛ መደበኛ ስብሰባው ዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተደረገውን የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ለማፅደቅ በተዘጋጀው አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ከዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተደረገው የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት የ1.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚያስገኝ ሲሆን…

የጥንቃቄ መልዕክት!
|

የጥንቃቄ መልዕክት!

ከክረምቱ ዝናብ ጋር ተያይዞ በአንድ አንድ የሃገራችን አካባቢዎች በደረሱ የመሬት መንሸራተትና የዉሃ ሙሌት ምክንያት የበርካታ ዜጎቻችን ሕይወት አልፏል፤ የአካል ጉዳትና የንብረት መውደም አደጋም ደርሷል፡፡በትናንትናው ምሽት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳ ግሽሬ ጉዱ ሞና ሆሞ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 (ስድስት) ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ የአካል…

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ቤተሰቦችና ማኅበረሰብን አጽናኑ

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ቤተሰቦችና ማኅበረሰብን አጽናኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እስካሁን የ231 ዜጎችን ሕይወት እንደቀጠፈ በተረጋገጠው የጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ቤተሰቦችና ማኅበረሰብ በአካል ለማፅናናት በስፍራው ተገኝተዋል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር። እና ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ ከቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ እንዲሁም ከሌሎች ከፍተኛ የፌደራል መንግሥት አመራሮች ጋር…

ወቅታዊ መረጃ

ወቅታዊ መረጃ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖችን በማሰብ ከነገ ሐምሌ 20 ቀን ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት ብሄራዊ የሃዘን ቀን ሆኖ እንዲታወጅ ወስኗል። በእነዚህ ቀናት በሁሉም የሃገሪቱ ግዛቶች፣ በኢትዮጵያ መርከቦች፣ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ፅህፈት ቤቶች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ…

የዲጂታል ስትራቴጂ አካታች ለሆነ የኢትዮጵያ ብልፅግና!

የዲጂታል ስትራቴጂ አካታች ለሆነ የኢትዮጵያ ብልፅግና!

ዓለም በአራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት ተጠቃሚነታችንን ለማረጋገጥ እና ወጣቱ በአዲሱ የዓለም ሥርዓት ውስጥ ስኬታማ እንዲሆን በንቃት መሥራት ይጠበቅብናል። በአሁኑ ወቅት እንደ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence)፣ ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ፣ ናኖ ቴክኖሎጂ እና ቢግ ዳታ ባሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የሚደገፉ የማምረት፣ የመገናኛ እና የአኗኗር ዘዬ ሽግግርን እየተመለከትን ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ ዲጂታል ከባቢ እና ቴክኖሎጂን…

የምጣኔ ኃብት ሪፎርም መነሻና አቅጣጫ

የምጣኔ ኃብት ሪፎርም መነሻና አቅጣጫ

ሀገር በቀል የምጣኔ ኃብት ማሻሻያ ሥራዎችአንደኛ በመንግሥት እጅ የነበሩትን የልማት ተቋማት ወደ ግሉ ዘርፍ ማስተላለፍ (Privatization)፣ ሁለተኛ የንግድ አሠራር ማሻሻያ (Ease of doing business) ሦስተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረትና የውጭ እዳ አከፋፈል ችግሮችን ለመፍታት የተሰሩ ማሻሻያዎች ናቸው።የግሉን ዘርፍ ከመንግሥት ጋር በጋራ ለማሳተፍ በወጣው አዋጅ የግሉ ዘርፍ እንዴት ተሳትፎ ማድረግ እንደሚችል መንግሥት ዝርዝር መረጃ ሰጥቷል። ትውልደ ኢትዮጵያውያን…

መንግሥት በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማዉን ጥልቅ ኀዘን ይገልጻል፡፡

መንግሥት በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማዉን ጥልቅ ኀዘን ይገልጻል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ ከሰሞኑ ባጋጠመው የመሬት መንሸራተት አደጋ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ በደረው ጉዳት የኢፌዴሪ መንግሥት የተሰማዉን ጥልቅ ኀዘን ይገልጻል፡፡ ለተጎጂ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶችም መፅናናትን ይመኛል፡፡ ባጋጠመው አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ተጎጂዎች ለመታደግ፣ በናዳ ውስጥ የተቀበሩ ሰዎችን ለማፈላለግ፣ የነብስ አድን ሥራዎችን ለማከናወን እንዲሁም ጉዳት የደረሰባቸዉን ዜጎች መልሶ…