የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውና በማህበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የቀረቡበት የምክክር መድረክ፤ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።
በዚህም ባለፉት ዓመታት በማህበራዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ወሳኝ ስኬቶች ቀርበዋል። በስምንት የለውጥ ዓመታት፤ ኢትዮጵያ በመሰረታዊና ማህበራዊ ዘርፎች የተስተዋሉ ክፍተቶች ላይ ትኩረት በማድረግ፤ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ሰፊ ሥርዓታዊ ሽግግር አድርጋለች። በትምህርት ዘርፍ አዲስ ሥርዓተ-ትምህርትን በመተግበር፣ የመማሪያ መጽሐፍት ስርጭትን በማሻሻል እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርትና የሀገር አቀፍ ፈተና ሥርዓቶችን በማዘመን፣ የትምህርት ዘርፉ ጥራትና ተዓማኒነት እንዲላበስ ተደርጓል። በተመሳሳይ የጤናው ዘርፍ ለ30…
