የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“ለህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይፋዊ አቀባበል ሥነሥርዓት አድርገናል። ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት ካደረግን በኋላ ከልዑካን ቡድኖቻችን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል። በውይይታችን በኢትዮጵያ እና ህንድ መካከል እያደገ የመጣውን ትብብር እና የወል ቅድሚያዎች የሚያንፀባርቁ አዳዲስ የትብብር መስኮችን ቃኘተናል። በሁለቱ ሀገራት መካከል በጉምሩክ የጋራ አስተዳደር ድጋፍ፣ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳታ ማዕከል ምስረታ የመግባቢያ ሥምምነቶችን እንዲሁም በአለምአቀፍ የሰላም ማስከበር ላይ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እና የሚያጠናክረውን የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ሥራ የመግባቢያ ሥምምነት የፊርማ ሥነሥርዓት ላይም ተገኝተናል። ህንድ የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አጋር ስትሆን የዛሬዎቹ ውይይቶች እና ሥምምነቶችም ለጋራ ጥቅም በተለያዩ ዘርፎች ያሉንን ትብብሮች ለማስፋት ያለንን የጋራ ቁርጠኛ አቋም ያሳያሉ።”

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

https://www.facebook.com/share/1FjkmbhZcb

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts